ቀን 04/08/2014 ዓ.ም ሁለተኛው ዙር የፈጠራ ሥራዎች ኤግዚቢሽን በጉራጌ ዞን በደቡብ ሶዶ ወረዳ በክላስተር ደረጃ መከበሩን የደቡብ ሶዶ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት አስታወቀ።

                                

በቀን 04/08/2014 ዓ.ም ማለትም በዕለተ ማክሰኞ በሁለት የት/ት ክላስተሮች የሳይንስና ፈጠራ ሥራዎች ኤግዚቢሽን ተከበረ፤ ኬላ ክላስተር የአንደኛው ክላስተር ስም ሲሆን በዚህም ክላስተር አራት ት/ቤቶችን በሥሩ የሚይዝ ሲሆን በዛሬው ዕለት የክላስተሩ ሱፐርቫይዘር የሆኑት መ/ር ዘነበ ጀማል ኤግዝቢሽኑን ለመሳተፍ የመጡ መምህራንና ተማሪዎችን የእንኳን ደህና መጣችሁ!!! እና የኤግዚቢሽኑን ዓላማና ግብ በተጨማሪም መልዕክቶችን በማስተላለፍ የኤግዚቢሽኑ መጀመር በይፋ አብስረው መርሐ ግብሩን ያስጀመሩ ሲሆን በዚህ ክላስተር ላይ ከተለያዩ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቶች የመጡት ተማሪዎች የሰሯቸውን የፈጠራ ሥራዎች እንዲያብራሩና እንዲያስጎበኙ ተደርገው በዚህ ክላስተር ላይ እስከ 19 የሚሆኑ የፈጠራ ሥራዎች ታይተዋል።

በመርሐ ግብሩ መጨረሻ አካባቢ ከተሳታፊዎች የኤግዚቢሽኑ ቆይታና የሚሰጣቸው አስተያየት ካለ ብለው የመድረኩ አስተባባሪና የክላስተሩ ሱፐርቫይዘር የሆኑት መ/ር ዘነበ ጀማል ዕድል የሰጡ ሲሆን ከኤግዚቢሽኑ ተሳታፊዎች ጠንካራና ገንቢ ሀሳቦችን ተነስተው፤ እንደ ጥያቄ የተነሱ ሀሳቦችን ደግሞ ከወረዳው ት/ቤቶች ፅ/ቤት የመምህራንና የት/ት አመራር ልማት ቡድን መሪ የሆኑት አቶ አውግቾ ከበደ እንዲሁም የወረዳው ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት ባለሙያዎች አቶ ሀብታሙ ባልቻ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ሥራዎች ክትትልና ድጋፍ አቅም ግንባታ ሥራ ሂደት አስተባባሪ እና አቶ ናትናኤል ይልማሽዋ የኢኮቴ መሠረተ ልማት ዝርጋታና አስተዳደር ሥራ ሂደት አስተባባሪ በተነሱት ሀሳቦችና ጥያቄዎች በተገቢው ሥልጠና በሚመስል መልኩ በማብራራት ሰፊ ትንተና ሰጥተዋል። በመጨረሻም ይህ ኤግዚቢሽን ቀጣይነት እንዳለው ከመድረኩ በማውሳት የዕለቱ መርሐ ግብር ተጠናቋል።

ሌላኛው ክላስተር ደግሞ ኬላ 2ተኛ ክላስተር የሚባል ሲሆን በዚህ ክላስተር ሦስት ት/ቤቶች የሚይዝ ሲሆን ነገር ግን አንደኛው ት/ቤት ገና በጅምር ላይ ያለ በመሆኑ በዚህ ክላስተር ተሳታፊዎች ሁለት ት/ቤቶች ነበሩ እነዚህም ኬላ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤትና ዳሙ ገነት ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ናቸው። በዚህ መርሐ ግብር ላይ የክላስተሩ ሱፐርቫይዘር የሆኑት መ/ር መለሰ ፋንታዬና የኑረና ኬላ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ርዕሰ መ/ር የሆኑት መ/ር ሻውል ወርቁ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የኤግዚቢሽኑ መጀመር በይፋ በማብሰር በኤግዚቢሽኑ ላይ በፈጠራ ሥራዎች ላይ ለመሳተፍ የመጡ ተማሪዎችን የሰሯቸውን የፈጠራ ሥራዎች እንዲያብራሩና እንዲያስጎበኙ አድርገዋል። በማኅበረሰቡ ዘንድ ያሉትን ችግሮች የሚፈቱ የፈጠራ ሥራዎች እስከ 18 የሚያህሉ በዚህ ክላስተር ላይ የታዩ ሲሆን በጉብኝት ወቅት በቀረቡት የፈጠራ ሥራዎች ላይ ግብዓት (ማሻሻያ) የሚሆኑ ሀሳቦችን የወረዳው ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ደመላሽ ውዴ ለተማሪዎቹ በመስጠት ጉብኝቱ ላይ እጅግ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል። በመጨረሻም በተሳታፊዎች ለቀረበላቸው ጥያቄና የግብዓት ሀሳቦች ላይ በመጀመሪያ የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት ባለሙያዎች የሆኑት አቶ ሀብታሙ ባልቻና አቶ ናትናኤል ይልማሽዋ በመቀጠልም የወረዳው ት/ቤቶች ፅ/ቤት ባለሙያ የሆኑት አቶ አውግቾ ከበደ ለቀረቡት ሀሳቦች ምላሽ የሰጡ ሲሆን የመርሐ ግብሩ አጠቃላይ ሁኔታዎች ላይ እንዲሁም በቀረቡ ሀሳቦች ላይ በአፅንዖት ምላሽ የሰጡት የወረዳው ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ደመላሽ ውዴ ሲሆኑ በኤግዚቢሽኑ በነበራቸው ቆይታ ድስተኛ እንደ ነበሩና ተሳታፊዎቹ ያነሷቿቸው ሀሳቦች እጅግ ገንቢና ተገቢ መሆኑን በማውሳት አክለውም ከዚህ ቀደም ማነቆ በነበሩት ችግሮች ምክንያት በርካታ ሥራዎች ሊሰሩ አለመቻላቸው ነገር ግን ከዚህ በኋላ ከባለድርሻ አካላት ትኩረት በመስጠት በጋራ የምንሰራው ጉዳይ ነው ሲሉ በመግለፅ እንዲሁም በርካታ ግንዛቤዎችን በማስጨበጥ መርሐ ግብሩ ተጠናቋል።










No comments:

Post a Comment

የደቡብ ሶዶ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት

  መግቢያ የወረዳው ሳይንስናኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ / ቤት የተቋቋመበት ዋናው ምክንያት በወረዳው የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በማልማትና በሁሉም ስፍራ በስፋት በመጠቀም የህብረተሰቡን ኑ...