🌀Credit Card ማለት እንደምናውቀው አይነት ATM Card ካርድ ሲሆን ምንጊዜም የራሱ ልዩ ቁጥር (Unique Number) ይኖረዋል።
🌀የፈለጋችሁት ሀገር ሄዳችሁ ካርዱን መጠቀም ትችላላችሁ፤ ለምሳሌ አንድ አሜሪካዊ ሀገራችን መጥቶ ገንዘብ ቢያንሰው የፈለገውን ያህል አውጥቶ መዝናናት፣ መክፈል ይችላል።
🌀አለም አቀፍ ክፍያዎችን ለመክፈል ያስችልዎታል።
🌀በአጭር ጊዜ ባለንብረት ያደርጋችኋል፤ ባወጣችሁት ገንዘብ መኪና፣ እንዲሁም ሌሎችንም እቃዎች መግዛት ያስችላችኋል።
🌀ብዙ ሀበሻ ሚሸወደው በዚህ ነው እዛ ሄዶ በትንሽ ፕላስቲክ ካርድ💳 እንዳሻው የፈለገውን መግዛት መቻሉን ሲያይ ኋላ እንደሚከፍል ይረሳና ይሸወዳል።
🌀እንደውም አብዛኛው የሄደበት ሀገር እንደሄደ የበተነውን ገንዘብ መክፈል ስለሚያቅተው፤ ባንኩም ያን ያህል ስለማይጫነው እንደቀልድ በእዳ ታስሮ 40 አመት ይቆያል (አንድ በቅርበት የማውቀው አርቲስት አለ እንደዚህ የሆነ)።
💠አሁን ከምንጠቀምበት ATM card ከ (Debit Card) በምን ይለያል?
🌀Debit card➡️ የምትጠቀሙት ባንክ አካውንታችሁ ውስጥ ያለውን ገንዘብ ያህል ብቻ ነው፤ Credit Card➡️ ሲሆን ግን ባንኩ እንደምትከፍሉት እርግጠኛ እስከሆነ ድረስ አካውንታችሁ ውስጥ ካለው የገንዘብ መጠን በላይ ይሰጣችኋል (ያበድራችኋል)
🌀Debit Card በአብዛኛው Visa® or Mastercard® logo ይኖረዋል።
🌀ከተበደራችሁ በኋላ በወር ውስጥ መክፈል ካልቻላችሁ ወለድ ይታሰባል።
🌀ሌላው ብዙ ሰው የሚሸወደው ባንኮቹ የሚገርም Information Retrieval System ይጠቀማሉ፤ ማን ምን ለመግዛት ገንዘቡን እንደሚያወጣ እያንዳንዷ ነገር Database ላይ ትመዘገባለች።
🌀ለምሳሌ፦ አቶ አበበ ከሱፐር ማርኬት ዳይፐርና ወተት ቢገዛ፤
አቶ በቀለ ደግሞ ቢራ ቢገዛና በወሩ ሁለቱም ሊበደሩ ቢመጡ የአቶ በቀለ በ % ስለሚወርድና ባንኩ በግለሰቡ ላይ ያለውን እምነት ስለሚያጣ የብድር መጠኑ ይወርዳል
🌀ሌላው ደግሞ ቅዳሜ ማታ እና ሰኞ ጠዋት ቢራ የገዛ እኩል አይታይም፤ ዳታቤዙ በካርዷ ከየትኛውም ሀገርና ቦታ የገዛችኋትን እያንዳንዷን ነገር ይመዘግባል።
🌀ስለዚህም Rating እንዳይወርድባችሁ እንደዚህ አይነት ነገር ስትገዙ በጥሬ ገንዘብ💵 መክፈል ተመራጭ ነው። @SSWSIT
No comments:
Post a Comment