ቀን 04/08/2014 ዓ.ም ሁለተኛው ዙር የፈጠራ ሥራዎች ኤግዚቢሽን በጉራጌ ዞን በደቡብ ሶዶ ወረዳ በክላስተር ደረጃ መከበሩን የደቡብ ሶዶ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት አስታወቀ።

                                

በቀን 04/08/2014 ዓ.ም ማለትም በዕለተ ማክሰኞ በሁለት የት/ት ክላስተሮች የሳይንስና ፈጠራ ሥራዎች ኤግዚቢሽን ተከበረ፤ ኬላ ክላስተር የአንደኛው ክላስተር ስም ሲሆን በዚህም ክላስተር አራት ት/ቤቶችን በሥሩ የሚይዝ ሲሆን በዛሬው ዕለት የክላስተሩ ሱፐርቫይዘር የሆኑት መ/ር ዘነበ ጀማል ኤግዝቢሽኑን ለመሳተፍ የመጡ መምህራንና ተማሪዎችን የእንኳን ደህና መጣችሁ!!! እና የኤግዚቢሽኑን ዓላማና ግብ በተጨማሪም መልዕክቶችን በማስተላለፍ የኤግዚቢሽኑ መጀመር በይፋ አብስረው መርሐ ግብሩን ያስጀመሩ ሲሆን በዚህ ክላስተር ላይ ከተለያዩ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቶች የመጡት ተማሪዎች የሰሯቸውን የፈጠራ ሥራዎች እንዲያብራሩና እንዲያስጎበኙ ተደርገው በዚህ ክላስተር ላይ እስከ 19 የሚሆኑ የፈጠራ ሥራዎች ታይተዋል።

በመርሐ ግብሩ መጨረሻ አካባቢ ከተሳታፊዎች የኤግዚቢሽኑ ቆይታና የሚሰጣቸው አስተያየት ካለ ብለው የመድረኩ አስተባባሪና የክላስተሩ ሱፐርቫይዘር የሆኑት መ/ር ዘነበ ጀማል ዕድል የሰጡ ሲሆን ከኤግዚቢሽኑ ተሳታፊዎች ጠንካራና ገንቢ ሀሳቦችን ተነስተው፤ እንደ ጥያቄ የተነሱ ሀሳቦችን ደግሞ ከወረዳው ት/ቤቶች ፅ/ቤት የመምህራንና የት/ት አመራር ልማት ቡድን መሪ የሆኑት አቶ አውግቾ ከበደ እንዲሁም የወረዳው ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት ባለሙያዎች አቶ ሀብታሙ ባልቻ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ሥራዎች ክትትልና ድጋፍ አቅም ግንባታ ሥራ ሂደት አስተባባሪ እና አቶ ናትናኤል ይልማሽዋ የኢኮቴ መሠረተ ልማት ዝርጋታና አስተዳደር ሥራ ሂደት አስተባባሪ በተነሱት ሀሳቦችና ጥያቄዎች በተገቢው ሥልጠና በሚመስል መልኩ በማብራራት ሰፊ ትንተና ሰጥተዋል። በመጨረሻም ይህ ኤግዚቢሽን ቀጣይነት እንዳለው ከመድረኩ በማውሳት የዕለቱ መርሐ ግብር ተጠናቋል።

ሌላኛው ክላስተር ደግሞ ኬላ 2ተኛ ክላስተር የሚባል ሲሆን በዚህ ክላስተር ሦስት ት/ቤቶች የሚይዝ ሲሆን ነገር ግን አንደኛው ት/ቤት ገና በጅምር ላይ ያለ በመሆኑ በዚህ ክላስተር ተሳታፊዎች ሁለት ት/ቤቶች ነበሩ እነዚህም ኬላ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤትና ዳሙ ገነት ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ናቸው። በዚህ መርሐ ግብር ላይ የክላስተሩ ሱፐርቫይዘር የሆኑት መ/ር መለሰ ፋንታዬና የኑረና ኬላ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ርዕሰ መ/ር የሆኑት መ/ር ሻውል ወርቁ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የኤግዚቢሽኑ መጀመር በይፋ በማብሰር በኤግዚቢሽኑ ላይ በፈጠራ ሥራዎች ላይ ለመሳተፍ የመጡ ተማሪዎችን የሰሯቸውን የፈጠራ ሥራዎች እንዲያብራሩና እንዲያስጎበኙ አድርገዋል። በማኅበረሰቡ ዘንድ ያሉትን ችግሮች የሚፈቱ የፈጠራ ሥራዎች እስከ 18 የሚያህሉ በዚህ ክላስተር ላይ የታዩ ሲሆን በጉብኝት ወቅት በቀረቡት የፈጠራ ሥራዎች ላይ ግብዓት (ማሻሻያ) የሚሆኑ ሀሳቦችን የወረዳው ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ደመላሽ ውዴ ለተማሪዎቹ በመስጠት ጉብኝቱ ላይ እጅግ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል። በመጨረሻም በተሳታፊዎች ለቀረበላቸው ጥያቄና የግብዓት ሀሳቦች ላይ በመጀመሪያ የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት ባለሙያዎች የሆኑት አቶ ሀብታሙ ባልቻና አቶ ናትናኤል ይልማሽዋ በመቀጠልም የወረዳው ት/ቤቶች ፅ/ቤት ባለሙያ የሆኑት አቶ አውግቾ ከበደ ለቀረቡት ሀሳቦች ምላሽ የሰጡ ሲሆን የመርሐ ግብሩ አጠቃላይ ሁኔታዎች ላይ እንዲሁም በቀረቡ ሀሳቦች ላይ በአፅንዖት ምላሽ የሰጡት የወረዳው ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ደመላሽ ውዴ ሲሆኑ በኤግዚቢሽኑ በነበራቸው ቆይታ ድስተኛ እንደ ነበሩና ተሳታፊዎቹ ያነሷቿቸው ሀሳቦች እጅግ ገንቢና ተገቢ መሆኑን በማውሳት አክለውም ከዚህ ቀደም ማነቆ በነበሩት ችግሮች ምክንያት በርካታ ሥራዎች ሊሰሩ አለመቻላቸው ነገር ግን ከዚህ በኋላ ከባለድርሻ አካላት ትኩረት በመስጠት በጋራ የምንሰራው ጉዳይ ነው ሲሉ በመግለፅ እንዲሁም በርካታ ግንዛቤዎችን በማስጨበጥ መርሐ ግብሩ ተጠናቋል።










ውድ የቻናላችን ተከታታዮች ዛሬ ይዘን የቀረብነው ቴሌግራምን እንዴት አድርገን እንደምንቆልፈው ነው። app lock ሳንጠቀም በራሱ በቴሌግራም መቆለፍ ይቻላል።


 የሚክተሉትን መንገዶችን መጠቅም ፦

1 setting የሚለው ውስጥ እንገባለን።

2.privacy and security የሚለውን 

3.passcode lock የሚለውን ነክተን እንገባለን....

4.....ከዛም በመቀጠልም passcode lock እናበራዋለን።

5.pin(ባለ 4 ይለፍቃል) ይጠይቀናል......የምንፈልገውን ቁጥር እንስጠዋለን።

6. ሞልተን ከጨረስን በኋላ Auto lock የሚለው ውስጥ ገብተን የምንፍልገውን እንመርጣል....

7.በመቀጠልም ከመረጥን በኋላ ወደ ዋናው እንመለሳለን.....

8.ከዛም ቴሌግራም ከሚለው አጠገብ Unlock የነበረውን ወደ Lock እንቀይረዋለን።

9.በመጨረሻም ይሄ ሁሉ ካደረግን በኋላ ከቴሌግራም እንውጣለለን.....ከዛም ተመልሰን ስንገባ......የሞላነውን pin (ባለ 4 ይለፍቃል) ይጠይቀናል።.....

▒▓⇨→መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶት ስልኮቻችሁ ላይ ላሉ

     ❖ Contact

     ❖ Group and Channel share አድርጉለን ከምስጋና ጋር።                                                                @SSWSIT

mobile_internet_data_Saving


ሞባይል ዳታ በሚከፈትበት ጊዜ ካርድ ወይም የተሞላውን የዳታ ጥቅል በቶሎ የሚጨርስበት ምክንያትቶችና መፍትሔዎች:

ምክንያቶች :-

1. የሞባይል ዳታ ተከፍቶ ሲረሳና ሳይዘጋ ሲቀር

2. ኢንተርኔት ክፍት ሆኖ ከተለያዩ ደህረ ገፆች ላይ ቀጥታ ቪዲዮች ሲታዩ

3. System settings እና Applications በራሳቸው ጊዜ አፕዴት ሲያደርጉ

4. በሞባይሉ ላይ የሚገኙ አፕሊኬሽኖች ተጠቃሚው በማያቸው መንገድ ከበስተጀርባ ሲሰሩ

5. በሞባይል ስልኩ ውስጥ ቫይረስ ሲኖር

መፍትሔዎች :-

👉ሞባይል ዳታ ተከፍቶ ሲረሳና ሲቆይ እንደ ሶሻል ሚዲያና

ኦንላይን የሚሰሩ አፕሊኬሽኖች ከተጠቃሚው እይታ ውጪ

ስራቸውን ያከናውናሉ። በዚህ ጊዜ በሞባይሉ ላይ የተሞላው

ክሬዲት ሰዓት ይቀንሳል ወይም ያልቃል ስለዚህም ኢንተርኔት

ተጠቅመው ከጨረሱ በኋላ የሞባይሉን ዳታ ያጥፉ።

👉በሞባይል ዳታ ኢንተርኔት ከፍቶ ከተለያዪ ድህ ገፆች ላይ

በቀጥታ ቪዲዮ መመልከት የተሞላውን ካርድ መጠን በጊዜ

ከሚያሳጥሩት ነገሮች ወስጥ አንደኛው ሲሆን ለዚህም ዋነኛው

ምክንያት በኢንተርኔት ቪዲዮ ቀጥታ መመልከት የሚቆጥረው

የዳታ መጠን ከፍተኛ ስለሆነ ነው ስለዚህ ቪዲዮ ማየቱ ግዴታ

ከሆነ በ Vidmate እና በሌሉች ቪዲዮ ዳውሎደር

አፕሊኬሽኖች የቪዲዮ ይዘት በመቀነስ ጭኖ መመልከቱ ወጪን

ይቆጥባል።

👉System settings እና Application በራሳቸው ጊዜ አፕዴት ሲያደርጉ የተሞላውን ዳታ(ካርድ) ይወስዳሉ ታዲያ ይህን ለማስቀረት Free wifi ከተገኘ አፕዴት ማድረግ ይህ ማድረግ የማይቻል ከሆነ system settings አፕዴት እንዳያደርግ ማስቆም:

  👍Settings ----About----Software Update---

Automatic update የሚለውን ማጥፋት

Applications አፕዴት እንዳያደርጉ ከተፈለገ ደግሞ

-Google Play መክፈት.

- hamburger የሚመስለውን በለ ሶስት ሆሪዞንታል ምልክት

ያለበትንም አናት ላይ በስተግራ በኩል Settings በመንካት

Auto-update apps.- disable automatic app updates, የሚለውን በመክፈት እና በመምረጥ መዝጋት ይቻላል

👉በሞባይሉ ላይ የሚገኙ አፕሊኬሽኖች ተጠቀሚው በማያቸው መንገድ ከበስተጀርባ ሲሰሩ ከእይታ ውጪ በመሆን የክሬዲት መጠን ይቀንሳሉ ታዲያ ይህን ለመከላከል:

    👍Settings----

data usage ---Restricted Background data

የሚለውን መክፈት... ከዚህ ይበልጥ ደግሞ Mobile data

saver አፕሊኬሽኖች በመጫን መጠቀም

  👉በሞባይል ሰልክ ውስጥ ቫይረስ ሲኖር የተሞላውን ሞባይል

ዳታ ከመቅስፈት እድሜው እንዲያጥር ያደርጋል ብሎም ቫይረሱ በራሱ ጊዜ የሞባይሉን ኦፕሬቲንግ ሲስተም በማዘዝ ያለማንም ትዕዛዝ ዳታ ይከፍታል ዳውንሎድ ያደርጋል አላስፈላጊ ነገሮችና ማስታወቂያዋች ይለቃል ከዚህም የተነሳ በፍጥነት የሞባይል ካርድ( ዳታ ጥቅል) ይጨርሳል ይህ ነገር በሞባይሉ ላይ ቢከሰት አንቲ ቫይረስ በመጫ ሰካን ማድረግ ይህ መፍትሔ

የማይሆን ከሆነ ለባለሙያ ማሳየቱ ተገቢ ነው::


▒▓⇨→መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶት ስልኮቻችሁ ላይ ላሉ

     ❖ Contact

     ❖ Group and Channel share አድርጉለን ከምስጋና ጋር።                                                                @SSWSIT

⚠️ለሁሉም የዊንዶውስ XP - 10 ተጠቃሚዎች በሙሉ⚠️

 


በጣም አደገኛ የሆነ የኦፕሬቲንግ ሲስተም ክፍተት ተገኝቷል። ይህንም ለመከላከል ማስተካከያ በ Microsoft  ዛሬ የተለቀቀ ሲሆን ይህንን ክፍተት ለመከላከል ዊንዶው ኮምፒውተራችሁን "System is up-to-date" ቢልም እንኳን አፕዴት በማድረድ ኮምፒውተሮን ከዚህ አደገኛ ክፍተት መጠበቅ ይችላሉ።

ስለ ክፍተቱ ትንሽ ማብራሪያ

ይህ ክፍተት ስሙ "Print nightmare" የሚባል ሲሆን ፒሪንት ስፑለር የሚባል የክፍተት አይነት ነው። ይህ ክፍተት በሀከሮች:–

– የርቀት ቁጥጥር ኮድን በ ሲስተም ደረጃ መብት መቆጣጠር (ማለትም ከኮምፒውተሩ ተጠቃሚ በላይ በኮምፒውተሩ ላይ ቁጥጥር ይኖራቸዋል።)

– ይህም ለሀከሮቹ የኮምፒውተራችሁን ሙሉ አክሰስ

ይሰጣቸዋል።

– ፋይሎቻችሁን ማየት፣ መቆጣጠር፣ ማጥፋት ወዘተ ይችላሉ።

– ከሱም አልፎ በራሳችሁ ኮምፒውተር በፓስወርድ ሊቆልፉቧችሁ ይችላሉ።

▒▓⇨→መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶት ስልኮቻችሁ ላይ ላሉ

     ❖ Contact

     ❖ Group and Channel share አድርጉለን ከምስጋና ጋር።                                                              @SSWSIT

✳️ አስር የእስፔስ እውነታዎች


🌀1. ስፔስ ሙሉ በሙሉ ዝም ያለ ነው


በጠፈር ውስጥ ከባቢ አየር የለም ፣ ይህ ማለት ድምጽ መስማት የሚችልበት መካከለኛ ወይም መንገድ የለውም ማለት ነው።


🌀2. በእኛ የፀሐይ ስርዓት ውስጥ በጣም ሞቃት ፕላኔት 450 ° ሴ ነው።


ቬነስ በሶላር ሲስተም ውስጥ በጣም ሞቃታማ ፕላኔት ናት እና በ 450 ዲግሪ ሴንቲግሬድ አካባቢ አማካይ የወለል ሙቀት አላት ቬነስ ለፀሐይ ቅርብ የሆነች ፕላኔት እንዳልሆነ ያውቃሉ? ያ ሜርኩሪ ነው። ከዚያ ሜርኩሪ በጣም ሞቃታማ ይሆናል ብለው ያስባሉ ፣ ግን ሜርኩሪ ከባቢ አየር የለውም (የሙቀት መጠንን ይቆጣጠራል) ፣ ይህም ትልቅ መለዋወጥን ያስከትላል።


🌀3. ሙሉ የናሳ ስፔስ ሱት 12,000,000 ዶላር ያወጣል።


ጠቅላላው ልብስ አሪፍ $ 12m ዶላር ሲያስከፍል ፣ ከዚያ ወጪ 70% ለቦርሳ እና ለቁጥጥር ሞዱል ነው። ሆኖም ፣ ናሳ የሚጠቀምበት የጠፈር ተስማሚነት በ 1974 ተገንብቷል። እነዚህ በዛሬ ዋጋ ቢገዙ ኖሮ 150 ሚሊዮን ዶላር ይገመት ነበር!


🌀4. የፀሐይ ግዝፈት የፀሐይ ሥርዓቱን 99.86% ይይዛል።


ፀሐይ በፀሐይ ሥርዓታችን ውስጥ ካለው የጅምላ መጠን 99.86% የሚሆነው ከምድር 330,000 እጥፍ ያህል ነው። ፀሐይ አብዛኛው ሃይድሮጂን (ሶስት አራተኛ ዋጋ ያለው) እንደሆነች ቀሪው ግዝፈቱ ለሂሊየም እንደተመሰረተ ያውቃሉ? ፀሐይ ድምጽ ቢኖራት ከዚያ ሁሉ ሂሊየም ከፍ ያለ እና የሚጮህ ነበር?


🌀5. አንድ ሚሊዮን መሬቶች በፀሐይ ውስጥ ሊስማሙ ይችላሉ


ፀሀይ ትልቅ ናት ፣ በግምት 1.3 ሚሊዮን የሚሆኑት ምድሮች በውስጣቸው ሊስማሙ ይችላሉ  ወይም መሬቶች ክብ ቅርፃቸውን ከያዙ 960,000 ይጣጣማሉ። ግን ያንን የምድር ብዛት በዓይነ ሕሊናዎ ማየት ይችላሉ?



🌀6. በወተት መንገድ ውስጥ ከዋክብት ይልቅ በምድር ላይ ብዙ ዛፎች አሉ


በፕላኔቷ ምድር ላይ ሦስት ትሪሊዮን ገደማ ዛፎች አሉ ፣ እና ከ100-400 ቢሊዮን ከዋክብት መካከል ፣ በግምት ፣ በጋላክሲው ውስጥ።


🌀7. በማርስ ላይ ያለው ፀሀይ ሰማያዊ ይመስላል

በምድር ላይ በፀሐይ መጥለቂያ ውስጥ ቀለሞች የበለጠ አስገራሚ እንደሆኑ ሁሉ ፣ ናሳ እንደሚለው በማርስ ላይ ፀሐይ ስትጠልቅ ከቀይ ፕላኔቷ ለሚመለከቱ የሰው ታዛቢዎች ሰማያዊ ይመስላል። ጥሩ አቧራ በሰማዩ የፀሐይ ክፍል አቅራቢያ ሰማያዊውን የበለጠ visibilke ያደርገዋል ፣ የተለመደው የቀን ብርሃን ደግሞ የቀይ ፕላኔት የታወቀ የዛገ አቧራ ቀለም ለሰው ዓይን በጣም አስተዋይ ያደርገዋል።


🌀8. በምድር ላይ ካለው የአሸዋ ቅንጣቶች ይልቅ በዓለም ውስጥ ብዙ ኮከቦች አሉ።

አጽናፈ ሰማይ ከራሳችን ጋላክሲ “ሚልኪ ዌይ” በላይ ይዘልቃል ፣ ለዚህም ነው ሳይንቲስቶች በጠፈር ውስጥ ስንት ኮከቦችን ብቻ መገመት የሚችሉት። ሆኖም የሳይንስ ሊቃውንት አጽናፈ ሰማይ በግምት 1,000,000,000,000,000,000,000,000,000 ኮከቦችን ወይም ሴፕቲሊንን እንደያዘ ይገምታሉ። በምድር ላይ ያለውን እያንዳንዱን የአሸዋ ቅንጣት ማንም ሊቆጥረው የማይችል ቢሆንም ፣ በሃዋይ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች የተገመተው አጠቃላይ ግምቱ ሰባት ኩንታል ፣ አምስት መቶ ኳድሪሊዮን እህል አካባቢ ነው። ያ በጣም ትልቅ የአሸዋ ግንብ ነው!


🌀9. በቬኑስ ላይ አንድ ቀን ከአንድ ዓመት ይረዝማል።

ቬነስ ቀኑን ለማጠናቀቅ 243 የምድር ቀናት የሚወስድ ዘገምተኛ ዘንግ ማዞሪያ አለው። በፀሐይ ዙሪያ ያለው የቬኑስ ምህዋር 225 የምድር ቀናት ነው ፣ ይህም በቬኑስ አንድ ቀን በቬኑስ ከ 18 ቀናት ያነሰ ቀን ያደርገዋል።


🌀10. ከአልማዝ የተሠራች ፕላኔት ከምድር ሁለት እጥፍ ትበልጣለች “ሱፐር ምድር” የተባለው 55 Cancri e ፣ ምናልባትም በግራፋይት እና በአልማዝ ተሸፍኗል። ወደዚያች ፕላኔት ጉብኝት ማድረጉ ምናልባት እዚያ ለመድረስ ለሚያስፈልገው የ 12 ሚሊዮን ዶላር የጠፈር ልብስ ይከፍላል!!!                                                                                                                           @SSWSIT

💠 ATM Card እና Debit Card በምን ይለያል ?


🌀Credit Card ማለት እንደምናውቀው አይነት  ATM Card ካርድ ሲሆን ምንጊዜም የራሱ ልዩ ቁጥር (Unique Number) ይኖረዋል።


🌀የፈለጋችሁት ሀገር ሄዳችሁ ካርዱን መጠቀም ትችላላችሁ፤ ለምሳሌ አንድ አሜሪካዊ ሀገራችን መጥቶ ገንዘብ ቢያንሰው የፈለገውን ያህል አውጥቶ መዝናናት፣ መክፈል ይችላል።


🌀አለም አቀፍ  ክፍያዎችን ለመክፈል ያስችልዎታል።


🌀በአጭር ጊዜ ባለንብረት ያደርጋችኋል፤ ባወጣችሁት ገንዘብ መኪና፣ እንዲሁም ሌሎችንም እቃዎች መግዛት ያስችላችኋል።


🌀ብዙ  ሀበሻ ሚሸወደው በዚህ ነው እዛ ሄዶ በትንሽ ፕላስቲክ ካርድ💳 እንዳሻው የፈለገውን መግዛት መቻሉን ሲያይ ኋላ እንደሚከፍል ይረሳና ይሸወዳል።


🌀እንደውም አብዛኛው የሄደበት ሀገር እንደሄደ የበተነውን ገንዘብ መክፈል ስለሚያቅተው፤ ባንኩም ያን ያህል ስለማይጫነው እንደቀልድ በእዳ ታስሮ 40 አመት ይቆያል (አንድ በቅርበት የማውቀው አርቲስት አለ እንደዚህ የሆነ)።


💠አሁን ከምንጠቀምበት ATM card ከ (Debit Card) በምን ይለያል?


🌀Debit card➡️ የምትጠቀሙት ባንክ አካውንታችሁ ውስጥ ያለውን ገንዘብ ያህል ብቻ ነው፤  Credit Card➡️ ሲሆን ግን ባንኩ እንደምትከፍሉት እርግጠኛ እስከሆነ ድረስ አካውንታችሁ ውስጥ ካለው የገንዘብ መጠን በላይ ይሰጣችኋል (ያበድራችኋል)


🌀Debit Card በአብዛኛው  Visa® or  Mastercard® logo ይኖረዋል።


🌀ከተበደራችሁ በኋላ በወር ውስጥ መክፈል ካልቻላችሁ  ወለድ ይታሰባል።


🌀ሌላው ብዙ ሰው የሚሸወደው ባንኮቹ የሚገርም Information Retrieval System ይጠቀማሉ፤ ማን ምን ለመግዛት ገንዘቡን እንደሚያወጣ እያንዳንዷ ነገር  Database ላይ ትመዘገባለች።


🌀ለምሳሌ፦ አቶ አበበ ከሱፐር ማርኬት ዳይፐርና ወተት ቢገዛ፤ 

አቶ በቀለ ደግሞ ቢራ ቢገዛና በወሩ ሁለቱም ሊበደሩ ቢመጡ የአቶ በቀለ በ % ስለሚወርድና ባንኩ በግለሰቡ ላይ ያለውን እምነት ስለሚያጣ የብድር መጠኑ ይወርዳል 


🌀ሌላው ደግሞ  ቅዳሜ ማታ እና  ሰኞ ጠዋት ቢራ የገዛ እኩል አይታይም፤ ዳታቤዙ በካርዷ ከየትኛውም ሀገርና ቦታ የገዛችኋትን እያንዳንዷን ነገር ይመዘግባል።


🌀ስለዚህም  Rating እንዳይወርድባችሁ እንደዚህ አይነት ነገር ስትገዙ በጥሬ ገንዘብ💵 መክፈል ተመራጭ ነው።                                                                                                                      @SSWSIT

✳️ Facebook ላይ ማወቅ ያሉብን ጠቃሚ ነገሮች።💡


 🌀1 Facebook በ Data ስትጠቀሙ ብዙ ብር  እንዳይበላባቹ ለማድረግ።


💠 በመጀመሪያም ሶስት ሰረዟን በመንካት ወደታች ወረድ ትላላችሁ ከዛ Data saver የሚል አለ እሱን ስትነኩት Data saver mode የሚል አለ እሱን On በማድረግ ብር እንዳይበላባቹ ማድረግ ትችላላችሁ።


🌀2 Face book ላይ Game መጫወት ለምትፈልጉ ደሞ።


💠 አሁንም ቀላል ነዉ ስቴፑ ሶስት ሰረዟን ትነኩ እና ወረድ ስትሉ Game የሚል አለ እሱን ስትነኩት ሶስት አይነት አማራጭ ይመጣላችኋል ከዛ ሁለተኛ ላይ ያለዉን Play የሚለዉን ንኩት ከዛ እሱን ስትነኩት  የተለያየ ጌሞችን ያመጣላችኋል ከዛ መርጣችሁ መጫወት ነዉ። 


🌀3 Face book ፕሮፋይላችሁን አቆላለፍ ።


💠 በ መጀመሪያም ወደ Setting ትገባላችሁ ከዛ ወረድ ስትሉ Audience and Visibility የሚለዉ ስር Profile Locking የሚል አለ እሱን ስትነኩት ከታች ጋር Lock your profile የሚል ይመጣላችኋል እሱን በመንካት መቆለፍ ትችላላችሁ።


🌀4 Online ሆናችሁ ግን ሌላ ሰዉ Online መሆናችሁን እንዳያዉቁ ለማድረግ።


💠 ወደ Setting ትገቡና Audience and Visibility የሚለዉ ስር Active status የሚል አለ እሱን ስትነኩት Show when you're active የሚል ይመጣላችኋል እሱን off አድርጉት ከዛ ማንም ሰዉ Online መሆናችሁን አያዉቅም


🌀5 የ Social media አካዉንቶቻችንን ፕሮፋይላችን ላይ እንዴት ማስቀመጥ እንችላለን ?


💠 በመጀመሪያም ወደ ምንጠቀምበት Browser በመግባት www.Facebook.com በማለት Login አድርገን ወደ አካዉንታን እንገባለን ከዛ ወደ ፕሮፋይላችን እንገባለን ከዛ Edit public Details የሚለዉን እንነካለን ከዛ Links የሚል አዲስ Option ይመጣልናል እሱን ስንነካዉ ሌላ አማራጭ ሶስተኛ ቦታ ላይ ያመጣልናል Social links የሚል ያመጣልናል እሱን ስንነካዉ የተለያየ የ Social media ዝርዝር ያመጣልናል ከዛ የምንፈልገዉን መርጠን ከ ጎኑ የዛን አካዉንት ስም ሊሆን ይችላል Username በማስገባት መጠቀም እንችላለን ከዛ ከታች ጋር Save የምትለዋን መንካት እንዳይረሳ 

 Nb: ይሄን ሁሉ የምናደርገዉ በምንጠቀምበት Browser ነዉ።


🌀6 ወደፈለግነዉ ቋንቋ ለመቀየር 


💠 ወደ Setting እንገባለን ከዛ Preference የሚለዉ ስር Language የሚል አለ እሱ ስር ገብተን ወደ ፈለግነዉ ቋንቋ መቀየር እንችላለን ( አማርኛ , ኦሮምኛ ) ከምናቃቸዉ ዉስጥ የመሳሰሉትን ማግኘት እንችላለን ።


🌀7 እንዴት ማንም ሰዉ Tag እንዳያደርገን ማድረግ እንችላለን።


💠 ወደ Setting ከዛ Profile and tagging የሚለዉን እንነካለን ከዛ መጀመሪያ ላይ ያለዉን Who can post on your profile ? የሚለዉን እንነካለን ከዛ Friends ላይ ከነበረ Only me የሚለዉ ላይ በማድረግ ማንም ሰዉ Tag እንዳያደርገን ማድረግ እንችላለን ።

@SSWSIT

✳️ ሌላ ሰው የፌስቡክ አካውንታችሁን ሲጠቀም እንዴት ፌስቡክ በሞባይል ስልካችሁ ሚሴጅ (SMS) እንዲልክልን ማድረግ እንደምትችሉ እንይ:-

💠 ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መንገዶች ተጠቅማቹ ደህንነታቹን መጠበቅ ትችላላቹ:-


1. ውደ ፌስቡክ አካውንቶ ይግቡ...


2. የ ፌስቡክ “Settings”⚙️ ዉሰጥ ይግቡ....


3. ከዛም “Settings” ውሰጥ በ ግራ በኩል ከሚመጡት ምርጫዎች “Security & Login” የሚለውን ይምረጡ...


4. ቀጥሎ ከሚመጡት ምርጫዎች “Get Alerts About Unrecognize logins”🔔 የሚለውን ውስጥ እንገባለን...


5. “Text messages” ከሚለው ስር

“Edit" የሚለውን ክሊክ እናረጋለን...


6. በመቀጠል “Get Text Message Alerts At” የሚለው ጋር እንነካለን በመቀጠል ከታች Save ብለን እንወጣለን ማለት ነው።


💠 ቀደም ብለው ለ ፌስቡክ የሞባይል ቁጥሮን ያልሰጡ ከሆነ ግን “Connect Your Phone Number” የሚለውን ላይ በመግባት የሞባይል ቁጥሮን ያስገቡ ከዛም በሞባይሎ የሚላከውን ቁጥር በሚመጣው ሳጥን ውስጥ ያስገቡ (Verify) ያድርጉ ከዛም “Save Changes” የሚለውን ክሊክ ያድርጉና ይውጡ አለቀ፡፡

 ከአሁን በኋላ አካውንቶ በአዲስ "Browser" በተከፈተ ቁጥር ሚሴጅ ይላክሎታል።

@SSWSIT

በጉራጌ ዞን በደቡብ ሶዶ ወረዳ በክላስተር ደረጃ የፈጠራ ሥራዎች ውድድርና ኤግዚቢሽን መጀመሩን የደቡብ ሶዶ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት አስታወቀ።

በቀን 23/07/2014 ዓ.ም ማለትም በዕለተ አርብ በሁለት የት/ት ክላስተሮች የሳይንስና ፈጠራ ሥራዎች ኤግዚቢሽን ተከበረ፤ የአንደኛው ክላስተር ስም፦ ጎጌቲ ክላስተር የሚባል ሲሆን በዚህም ክላስተር አምስት ት/ቤቶችን አቅፎ የሚይዝ ክላስተር እንደሆነና በዛሬው ዕለት ከዚህ ክላስተር ኤግዚቢሽኑን ለመሳተፍ የመጡ ተማሪዎች የመክፈቻ ንግግር የክላስተሩ ሱፐርቫይዘር የሆኑት መ/ር ደበበ ታደሰ በማድረግ በዚህ ክላስተር ት/ቤቶች የጋራ የሆነ ልምድ የሚያገኙበትና ችግር ፈቺ የሆነ ፈጠራ ጎልቶ የሚታይበት እንደሆነ በማውሳት አክለውም በዚህ ኤግዚቢሽን ተማሪዎች ከተለያየ ት/ቤት በመጡ ተማሪዎች የሚያገኟቸው እውቀት፣ ክህሎት እንዲሁም ልምድ ቀላል እንዳይደለ በመግለፅ ይህን ዕድል በዋዛ መመልከት እንደሌለባቸው በማሳሰብ የኤግዝቢሽኑ መጀመር ይፋ በማድረግ የፈጠራ ሥራዎች እንዲጎበኙ እና ተማሪዎች በሰሯቸው የፈጠራ ሥራዎች ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡ ተደርጓል። በተጨማሪም በዚህ ክላስተር እስከ 40 የሚሆኑ የፈጠራ ሥራዎች የታዩበትና ዕለቱም በጥያቄና መልስ ውድድር እንዲሁም በውይይት ተከብሮ ውሏል። 

 በፕሮግራሙ ማጠቃለያ ላይ የደቡብ ሶዶ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት በሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ሥራዎች ባለሙያ ተወክለው የተገኙት የፅ/ቤቱ ባለሙያ የሆኑት አቶ ናትናኤል ይልማሽዋ በቀረቡት የፈጠራ ሥራዎች ላይ በልጆቹ አቅምና ደረጃ አንፃር አድናቆታቸውን በመቸር ከዚህም በላይ መስራትና ማደግ እንደሚቻል የገለፁ ሲሆን በተሳታፊዎች ለቀረበላቸው አስተያየቶች ተገቢውን ምላሽና ተሞክሮ በመስጠት ንግግራቸውን ቋጭተዋል። በጎጌቲ ክላስተር የኤግዚቢሽኑ የመጨረሻ መርሐ ግብር የነበረው በፈጠራ ሥራዎች ለተሳተፉ ተማሪዎችና ለየት/ቤቱ የፈጠራ ሥራ ክበባት የምስክር ወረቀት በመስጠት ፕሮግራሙ ተጠናቋል።

በሁለተኛው ክላስተር ደግሞ፦ ጎሴ ሳለን ክላስተር የሚባል ሲሆን በዚህም ክላስተር አራት ት/ቤቶችን አቅፎ የሚይዝ ክላስተር እንደሆነና በዛሬው ዕለት ከዚህ ክላስተር ኤግዚቢሽኑን ለመሳተፍ የመጡ ተማሪዎች የመክፈቻ ንግግር ከወረዳው የት/ቤቶች ፅ/ቤት ተወክለው የተገኙት አቶ አውግቾ ከበደ በማድረግ በዚህ ክላስተር ት/ቤቶች የጋራ የሆነ ልምድ የሚያገኙበትና ችግር ፈቺ የሆነ ፈጠራ የሚንፀባረቅበት እንደሆነ በማውሳት በተጨማሪም በዚህ ኤግዚቢሽን ተማሪዎች ከተለያየ ት/ቤት በመጡ ተማሪዎች የሚያገኟቸው እውቀት፣ ክህሎት እንዲሁም ልምድ እንደሚጠቅማቸው በመግለፅ የኤግዝቢሽኑ መጀመር ይፋ በማድረግ የፈጠራ ሥራዎች እንዲጎበኙ እና ተማሪዎች በሰሯቸው የፈጠራ ሥራዎች ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡ ተደርጓል። በተጨማሪም በዚህ ክላስተር እስከ 33 የሚሆኑ የፈጠራ ሥራዎች የታዩበትና ዕለቱም በጥያቄና መልስ ውድድር እንዲሁም በውይይት ተከብሮ ውሏል። በፕሮግራሙ ማጠቃለያ ላይ የደቡብ ሶዶ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት በሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ሥራዎች ባለሙያ የሆኑት አቶ ሀብታሙ ባልቻ በቀረቡት የፈጠራ ሥራዎች ላይ ከዚህም በላይ መስራትና ማደግ እንደሚቻል የገለፁ ሲሆን በተሳታፊዎች ለቀረበላቸው አስተያየቶች ተገቢውን ምላሽና ተሞክሮ በመስጠት ንግግራቸውን ቋጭተዋል። በጎሴ ሳለን ክላስተር የኤግዚቢሽኑ የመጨረሻ መርሐ ግብር የነበረው በፈጠራ ሥራዎች ለተሳተፉ ተማሪዎችና ለየት/ቤቱ የፈጠራ ሥራ ክበባት የምስክር ወረቀት በመስጠት ፕሮግራሙ ተጠናቋል። በፅ/ቤቱ ባለሙያዎች በቀረበላቸው ሪፖርት መሠረት የደቡብ ሶዶ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ደመላሽ ውዴ ይሄ ጅምር እንደሆነና በቀጣይ ከት/ቤቶች ፅ/ቤት ጋር በመተባበር በወረዳ ደረጃ እንደሚከበር በማውሳት በተጨማሪም የፈጠራ ሥራዎቹ በቴክኖሎጂ የታገዙ እንዲሆኑና ከዛም ልቆ የማኅበረሰቡ ችግር እንዲፈታ ፅ/ቤታቸው የቴክኒካል ድጋፍ እንደሚያደርግ አሳስበው ኤግዚቢሽኑን ያከበሩ ት/ቤቶች በማመስገን ሀሳባቸውን አጠናቀዋል።

'image.png' failed to upload. TransportError: There was an error during the transport or processing of this request. Error code = 103, Path = /_/BloggerUi/data/batchexecute
'image.png' failed to upload. TransportError: There was an error during the transport or processing of this request. Error code = 103, Path = /_/BloggerUi/data/batchexecute
Uploading: 1365315 of 1365315 bytes uploaded.






የደቡብ ሶዶ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት

  መግቢያ የወረዳው ሳይንስናኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ / ቤት የተቋቋመበት ዋናው ምክንያት በወረዳው የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በማልማትና በሁሉም ስፍራ በስፋት በመጠቀም የህብረተሰቡን ኑ...