የአይፎን 13 የሳተላይት ግንኙነቶችን እንደ አማራጭ ይዞ እንደሚመጣ ተነገረ፡፡


 

የአይፎን 13 የሳተላይት ግንኙነቶችን እንደ አማራጭ ይዞ እንደሚመጣ ተነገረ፡፡

በመስከረም ወር ለገበያ እንደሚቀርብ የሚጠበቀው አዲሱ የአፕል ኩባንያ ምርት አይፎን 13 የሳተላይት ግንኙነቶችን እንደ አማራጭ ይዞ እንደሚመጣ ተነገረ፡፡

የቴሌኮም አገልግሎቶች ተደራሽ በማይሆኑባቸው አካባቢዎች በታችኛው የመሬት ምሕዋር የሚገኙ ሳተላይቶችን በመጠቀም የድምፅ እና የአጭር መልዕክት አገልግሎቶችን ተደራሽ ማድረግ እንደሚችል ሲኔት ዘግቧል፡፡

አዲሱ ስልክ በሳተላይት አማካኝነት አገልግሎት መስጠት የሚያስችለው Qualcomm X60 የተባለ ቺፕ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ይህ አዲስ ገፅታ ከቴሌኮም አገልግሎቶች ርቀው ለሚኖሩ እና መሰል አገልግሎቶች ተደራሽ ባልሆኑባቸው አካባቢዎች የሚጓዙ ተጠቃሚዎችን ትኩረት እንደሚያገኝ ይጠበቃል፡፡ (Cnet, AICE)

 


🚩 YouTube የDislike Buttonኑን ከPublic እይታ ወደ Private ሊቀይር ነው ይሄም ማለት YouTube ላይ የሚለቀቅ ማንኛውንም Video ተመልካቹ ወይም አንድ ግለሰብ Dislike ቢያደርግ የዛን የDislike መጠን ሌሎች ሰዎች ማየት አይችሉም ለChannleሉ ባለቤት ብቻ ይታያል ማለት ነው.. YouTube ይሄንን ያደረገበት ምክንያት (Dislike Attackን) ለመከላከል ነው Dislike Attack ማለት አንዳንድ ሰዎች በግልም በGroupፕም በመሆን ሆን ብለው አንዳንድ የYouTube Channelሎችን ኢላማ   በማድረግ እዛ Channle ላይ የሚለቀቁትን Video Dislike ያደርጋሉ ይሄ ደግሞ የChannel Creatorች ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ በመሆኑ ነው።

🛑 ከቻርጅጋ የተገናኙ ችግሮች

 



🛑 ከቻርጅጋ የተገናኙ ችግሮች
♻️ ስልኩን ቻርጅ ስናደርገው የሚሞቅ ከሆነ test አድርጎ መለየት cap_diode ሁለቱም ሰላም ከሆኑ charge Ic መቀየር።
♻️ ቻርጀሩ ቻርጅ እያደረገ ስልኩ አልሞላ ካለ cap & diode check ማድረግ ዝም ብሎ ጃርጅ የሚያደርግ ከሆነ ባትሪ connectrun ማጽዳት ወይም አስተካክሎ መበየድ።




♻️ ቲክቶክ ለወደድነው ቪዲዮ ገንዘብ ቲፕ የምናደርግበት አማራጭ እየሞከረ መሆኑን አስታወቀ።

 


♻️ ቲክቶክ ለወደድነው ቪዲዮ ገንዘብ ቲፕ የምናደርግበት አማራጭ እየሞከረ መሆኑን አስታወቀ።


አዲሱ የቲክቶክ አገልግሎትም በማህበራዊ ትስስሩ ላይ ተጭነው ለወደድነው ምስል ጉርሻ ገንዘብ (ቲፕ) ለመስጠት የሚያስችል መሆኑም ነው የተነገረው። “ቲፕ (tips)” የሚል አማራጭ የሚመጣው አዲሱ አገልግሎት 5፣ 10 እና 15 ዶላር ቲፕ ማደረግ ያስችላል ሲል ዘ ቨርጅ የተባለው ድረ ገፅ አስነብቧል።


ከአማራጮቹ ውጪም ቲፕ ማድረግ የሚፈልግ ሰው ዝቅተኛ ተብሎ ከተቀመጠው 1 ዶላር ጀምሮ እስከፈለገው የገንዘብ መጠን ድረስ ቲፕ ማድረግ የሚችል መሆኑም ታውቋል። በቲክቶክ ላይ በጉርሻ መልክ (ቲፕ) የተሰጠው ገንዘብ ሳይቆራረጥ ለባለ ተንቀሳቃሽ ምስሉ (ቪዲዮ ባለቤት) የሚደርስ መሆኑም ነው የተሰማው።


በቲክቶክ ላይ የጉርሻ (ቲፕስ) ተጠቃሚ ለመሆን ተጠቃሚዎች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች እንዳሉም ኩባንያው አስታውቋል። ከመስፈርቶቹ ውስጥ ተጠቃሚው ቢያንስ 100 ሺህ ተከታዮች ያሉት ሊሆን ይገባል የሚለው ዋነኛው ሲሆን፤ የቲክቶክ የእድሜ መስፈርት ማሟላትም ሌለኛው ነው ተብሏል።


በቲክቶክ ላይ ቲፕ የሚያደርግ ወይም ጉርሻ የሚሰጥ ሰው እድሜው ከ18 ዓመት በላይ መሆን አለበት የሚለውንም ኩባያው በመስፈርትነት አስቀምጧል። የቲክቶክ ቲፕ አገልግሎት አሁን ላይ በሙከራ ደረጃ የተሰወኑ ገጾች ላይ ብቻ መለቀቁ የነገረ ሲሆን፤ በምን ያክል ስፋት እና መቼ ሙሉ በሙሉ ይለቀቃል የሚለው ላይ ግን ኩባያው አስተያየት አልሰጠም።Visit it!!!

 📍የሳምንቱ Technology News📍

፩ YouTube የDislike Buttonኑን ከPublic እይታ ወደ Private ሊቀይር ነው ይሄም ማለት YouTube ላይ የሚለቀቁትን ማንኛውንም Video ተመልካቹ ወይም ግለሰብ Dislike ቢያደርግ ያን Dislike ሌሎች ሰወች ማየት አይችሉም ለChannleሉ ባለቤት ብቻ ይታያል ማለት ነው 👁


YouTube ይሄንን ያደረገበት ምክንያት (Dislike Attackን) ለመከላከል ነው Dislike Attack ማለት አንዳንድ ሰወች በግልም በGroupፕም በመሆን ሆን ብለው አንዳንድ የYouTube Channelሎችን ኢላማ   በማድረግ እዛ Channle ላይ የሚለቀቁትን Video Dislike ያደርጋሉ ይሄ ደግሞ የChannel Creatorች ላይ ከፍተኛ ጮና እያሳደረ በመሆኑ ነው🤕 


፪ የGoogle ኩባንያ ምርት የሆኑት Pixel 6 ና 6 Pro ስልኮች ካሜራቸውን በመጠቀም የስልኩን ባለቤት የልብና የትንፋሽ መጠንን የሚለካ ና የሚከታተል Feature ይዞ መቷል🔥


፫ Apple ና Microsoft ሁለቱም በአሁኑ ጊዜ ዋጋቸው 2.5 ትሪሊዮን💲አካባቢ ነው 😬


፬ የYouTube የማስታወቂያ ገቢው በሦስተኛው ሩብ ዓመት 7.2 ቢሊዮን ዶላር አድርሷል📉


፭ Gmail በአንዳንድ ሀገራት የመቆራረጠ ችግር ገጥሞታል ብዙ ተጠቃሚወችም ችግሩን ለ Google Report እያደረጉ ነው በUS UK ና Europe ያሉ ሰወች የGmail አካውንታቸውን Login ለማድረግ እየተቸገሩ ነው


Google ችግሩን Fix ለማድረግ ተፍ ተፍ እያለ ይገኛል።


የሳይበር ደህንነት ስርዓቶችን ፣ አውታረ መረቦችን እና ፕሮግራሞችን ከዲጂታል ጥቃቶች የመጠበቅ ተግባር ነው፡፡ 
እነዚህ የሳይበር ጥቃቶች ብዙውን ጊዜ ሚስጥራዊ መረጃዎችን ለመድረስ፣ ለመለወጥ ወይም ለማጥፋት ያተኮሩ ናቸው ፡፡ ከተጠቃሚዎች ገንዘብ ማጭበርበር ወይም መደበኛ የንግድ ሥራዎችን ማቋረጥ ነው፡፡
      ---- ---ዘዴ---------   
የሳይበር ደህንነት ለመጠበቅ     
          ------ ----
1.ከማይታወቁ  ምንጮች application download በአንድሮይድ ስልክ ወይም ታብሌት ላይ በተንኮል አዘል ዌር ለመበከል ቀላሉ መንገድ application ከ Google Play app store ውጭ መጫን መጀመር ነው ፡፡ በማንኛውም መደበኛ የ Android setting ውስጥ ‘unofficial’  ያልሆኑ app መጫን የሚያስችል እና የሚያሰናክል አመልካች ሳጥን disable ማደርግ፡፡ ራሱን ሕጋዊ የሚያደርግ አንድሮይድ በጣም ደህንነቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
 2. Upgrade to Android 3.0   or above የመጀመሪያው የ Android file system ከሞላ ጎደል ለሦስት ዓመታት ያህል Android 3.0 ነበር። ምንም ዓይነት የመረጃ encryption  የማይጠቀሙ መሣሪያዎች file መጥፋትን ለመጉዳት በጣም የተጋለጡ ናቸው፡፡  3.ደህንነታቸው ካልተጠበቀ ፣ የማይታወቁ የ Wi-Fi  አውታረ መረቦች ጋር አይገናኙ ደህንነቱ ያልተጠበቀ የ Wi-FI አውታረ መረብ ነፃ የበይነመረብ free ሊመስል ይችላል ፣ ግን በተለይ ጊዜ ያለፈበትን የ Android system የሚጠቀሙ ከሆነ አደገኛ ሊሆን ይችላል። አስመሳይ የ Wi-Fi አውታረ መረቦች‹middleman’›ጥቃት(attack,) ለማዘጋጀት ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ ፣ የትኛውም የግብዓት መረጃ በሶስተኛ ወገን ሊጠለፍ ይችላል - የይለፍ ቃሎችን እና እንደ የክሬዲት ካርድ ቁጥሮች ያሉ የግል ዝርዝሮችን ጨምሮ ፡፡  
 4. የርቀት መቆለፊያ Install a remote/lock app ይጫኑ Android ስልኮ ከጠፋ ወይም ከተሰረቀ የሚጠርገው ወይም የሚቆልፍበት መንገድ መኖሩ አስተዋይነት ነው ፡፡ ከ  web interface ወይም በፅሁፍ በኩል ለሚሰጡት ትዕዛዝ ምላሽ የሚሰጡ apps ከ Google Play የሚገኙ ይህንኑ የሚያደርጉ apps አሉ ፡፡ ታዋቂ የርቀት መጥረጊያ እና የመቆለፊያ apps Cerberus እና Avast  ሞባይል ደህንነት ያካትታሉ።
5.ሁሉንም ሚስጥራዊነት ያላቸውን መረጃዎች(Data) ከተጨማሪ Encryption (password) በስልኩ ወይም Tablet ላይ logged information በአጠቃላይ ማስታወሻ ውስጥ ስሱ መረጃዎችን መመዝገቡ መጥፎ ሀሳብ ነው። በይለፍ ቃል(password) እና encryption.  ጀርባ መረጃን የሚያከማቹ ብዙ application አሉ። ከፍተኛ ምርጫዎች Secure እና File Hide Expert ን ያካትታሉ፡፡ 6. የሚላክ SMS  & link ይገንዘቡ ፕሪሚየም የ SMS ማስፈራሪያዎች በ Android ተንኮል አዘል sms ውስጥ ለሚከሰት ጭማሪ በከፊል ተጠያቂ ናቸው። በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ወደ ብርሃን የወጣው የኦባድ(Obad) ማስፈራሪያ ዋና ተመን የsms ጽሑፎችን መላክ ፣ ሌሎች ተንኮል አዘል App መጫን እና ሌላ ኮድ ማስፈፀም ይችላል ፡፡ በስልክ ሂሳብ ላይ ምስጢራዊ እንቅስቃሴ ካለ ፣ ወደዚህ ዓይነት ጥቃት እንዳይደረሰ ያረጋግጡ ፡፡
#ጠቃሚ የሆኑ ነገሮች ቶሎ ቶሎ እንዲለቀቅሎት ከናንተ
የሚጠበቀው share
በማድረግ
የበለጠ እንድንሰራ Moral ሁኑን! ለጓደኛዎ


 








 ☞በአለማችን ይኖራሉ ብለው የማይገምቷቸው አስገራሚ ድረ ገፆች




✔️✔️✔️✔️✔️✔️✔️✔️✔️✔️✔️


☞ በአሁኑ ወቅት መጠኑ ይለያይ እንጂ አንዳንዶቻችን በየቀኑ የኢንተርኔት መረቦችን መቃኘታችን የተለመደ ተግባር ሆኗል።


የምንቃኛቸው ድረ ገፆችም ብዙ ጊዜ የምናውቃቸውን አልያም በጣም ታዋቂዎቹን ነው።


አንዳንድ ጊዜም በፌስቡክ አማካኝነት ያገኘናቸው መረጃዎች አዳዲስ ድረ ገፆችን ያስተዋውቁናል።


እነዚህን አዳዲስ ድረ ገፆችም ጠቃሚ ሆነው ስናገኛቸው ለሌላ ጊዜ እንድንጠቀማቸው ቡክማርክ አድረገን እናስቀምጣቸዋለን።


ከዚህ በታች የተዘረዘሩት 9 ድረ ገፆች ግን ምናልባትም አይተናቸው የማናውቃቸው እና የተለየ አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው ይላል ቴክወርም የተሰኘው የቴክኖሎጂ ድረ ገፅ ዘገባ።


1. 10Minutemail.com


ይህ ድረ ገፅ ለ10 ደቂቃ የሚቆይ የኢሜል አድራሻ ለመክፈት ያስችላል።


ድረ ገፁ የተላላክናቸውን መልዕክቶች እና የኢሜል አድራሻውን ከ10 ደቂቃዎች በኋላ ሙሉ በሙሉ ያጠፋዋል።


10Minutemail.com እንደከፈትነው ምንም ምዝገባ ሳያስፈልገን ራሱ የኢሜል አድራሻ ይሰጠናል።

👇👇👇👇

በተጨማሪም Tempmail ለዚህ ይጠቅመናል አጠራጣሪ ድረገጾች ስንከፍት ኢሜል ሲጠይቁን በዚህ መጠቀም እንችላለን


2. የሀሰት ስም እና አድራሻ ፈጣሪ - Fake Name Generator


በጣም አይነአፋር የሆኑ፣ የግል ጉዳያቸው የሚያስጨንቃቸው እና ትክክለኛ ስማቸውን ይፋ ማድረግ የማይፈልጉ ሰዎች በዚህ ድረ ገፅ አማካኝነት የሀሰት ስም እና ዝርዝር መረጃዎችን መፍጠር ይችላሉ።


Fakenamegenerator.com  


3. አንዳንድ ድረ ገፆች የማይከፍቱት እንዳልከፍታቸው ስለታገድኩ ነው ወይስ ስለማይሰሩ? - Down for Everyone or Just Me


አንዳንድ ጊዜ ኮምፒውተርዎ የተወሰኑ ድረ ገፆችን አልከፍት ሊልዎት ይችላል። እናም በዚህ ድረ ገፅ አማካኝነት እውን ይህ ድረ ገፅ አልከፍት ያለዎት ስለማይሰራ ነው አልያስ ሆን ተብሎ እንዳይከፍቱት ስለተደረገ ነው የሚለውን ማረጋገጥ ይችላሉ።


Downforeveryoneorjustme.com 


4. የቀናት ልዩነትን ለማስላት - Date and Time 


በዚህ ድረ ገፅ ደግሞ በቀናት እና አመታት መካከል ያሉ ልዩነቶችን ለማስላት ይጠቅማል።


ለአብነትም እድሜያችን በቀናት ለማስላት የተወለድንበትን ቀን፣ ወር እና አመት እና የእለቱን ቀን ወር እና አመት በማስገባት በምድር ላይ ለስንት ቀናት ቆይታ እንዳደረግን ማስላት እንችላለን።


የምናሰላው ቀን በአላትን እና ቅዳሜ እና እሁድን አካቶ አልያም ሳያካትት ስንት እንደሆነም ማወቅ ያስችላል።


timeanddate.com 


5. የድረ ገፆችን የፊት ገፅ ምስል ለማስቀረት - Web Capture


የተለያዩ ድረ ገፆችን የፊት ገፅታ ምስል ለማስቀረት እና ወደ JPG/JPEG፣ PNG አልያም PDF ፎርማት ለመቀየር ይህን ድረ ገፅ ይጠቀሙ። 


webcapture.net/  


6. ጎግልን ያለምንም የሀገር ገደብ ለመጠቀም - Google NCR


የጎግል ድረ ገፅን (google.com) ስንከፍት ጎግል ወደየሀገራችን ዶሜን ያስገባናል። ለምሳሌ ጎግልን በኢትዮጵያ ስንከፍት google.com.et ወደሚለው ያሸጋግረናል። ይህም የሚሆነው ጎግል እንደየሀገራቱ የሚከለክለው እና የሚፈቅደው ስላለው ነው።


እናም ጎግልን ያለምንም የሀገራት ገደብ ለመክፈት google.com/ncr ብለን መፈለግ በቂ ነው።


7. የተላኩልን ፋይሎች በቫይረስ የተጠቁ መሆን አለመሆናቸውን ለማረጋገጥ -የተላከልን Virustotal


ከጓደኞቻችን አልያም ከማናውቀው ግለሰብ የሚያጠራጥር ፋይል ከተላከልን እና ከኢንተርነየት በቀጥታ ካወረድነው በዚህ ድረ ገፅ አማካኝነት  ፋይል ቫይረስ መያዙን እና አለመያዙን ማወቅ እንችላለን።


ቪሩስቶታል ነፃ የኢንተርኔት የቫይረስ መመርመሪያ (ስካነር) ነው።


8. በአለማችን እየተከናወኑ ያሉ ወቅታዊ የመረጃ ዘረፋዎችን የሚያሳይ ካርታ - IPviking


በአለም ዙሪያ እየተከናወኑ ያሉ የመረጃ ምንተፋዎች፣ የአይፒ አድራሻዎች፣ የመረጃ ዘራፊዎቹን አድራሻ እና የመሳሰሉ መረጃዎችን http://map.norsecorp.com/#/ በተባለው ድረ ገፅ ላይ መመልከት ይቻላል።


9. Hackertyper


ይህን ድረ ገፅ ከፍተን የተለያዩ ፊደላትን እና ቁጥሮችን ስንጫን መረጃ ዘራፊዎች የሚጠቀሙበትን አይነት ገፅ ይከፍትልናል።


በዚህም ጓደኞቻችን እና ወዳጆቻችን የተለያዩ ድርጅቶችን መረጃዎችን እየሰረቅን ለማስመሰልና ለመሸወድ እንችላለን።


http://hackertyper.net/


10. Password Generator 


ጠንካራ  እና በቀላሉ ብሬክ የማይደረግ የይለፍ ቃል ለፌስቡክ ለኢሜል ለሌሎች ፓስወርድ ለሚጠይቁ በሙሉ ጠንካራ የይለፍ ቃል (ፓስወርድ)  ለመመስረት

 📲 ስልክዎ እንደተጠለፈ የሚያሳዩ ሰባት ምልክቶች

 ▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃


1. የስልክዎ ፍጥነት ከቀነሰ


ተንቀሳቃሽ ስልክዎ ከሌላው ጊዜ በተለየ ትዕዛዞችን ለማከናወን ረዘም ያለ ጊዜ የሚፈጅ ከሆነ፤ ባዕድ ሶፍትዌሮች (ማልዌር) እያስቸገሩት ነው ማለት ነው።


እነዚህ ማልዌር የተባሉት ቫይረሶች ዋነኛ ሥራቸው የስልክዎን አጠቃላይ እንቅስቃሴ ማዘግየት ሊሆን ስለሚችል፤ በአፋጣኝ ማስወገድ ተገቢ ነው።


2. ስልክዎ በጣም የሚግል ከሆነ


ስልክዎት ከተለመደው ከፍ ባለ ሁኔታ የሚግል ከሆነ፤ ችግር አለ ማለት ነው። በፍጥነት እርምጃ ይውሰዱ አልያም ባለሙያ ያማክሩ።


3. የስልክዎ የባትሪ ኃይል ቶሎ የሚያልቅ ከሆነ


ስልክዎ ከፍተኛ ሙቀት አለው ማለት ደግሞ የባትሪው ኃይል ቶሎ ቶሎ ያልቃል ማለት ነው።


ምናልባት ስልክዎ አዳዲስ መተግበሪያዎችንና ሶፍትዌሮችን ለማደስ በሚሞክርበት ወቅት የባትሪውን ኃይል ሊጨርስ ይችላል። ነገር ግን ምክንያቱ ይህ ካልሆነ ስልክዎ ተጠልፎ ሊሆን እንደሚችል ማሰብ አለብዎ።


4. ወደ ማያውቁት ሰው መልዕክት ከተላከ ወይም ከማያውቁት ሰው መልዕክት ከደረስዎ


ብዙ ጊዜ እርስዎ የማያውቋቸው መልእክቶች የሚላኩት በዋትሳፕና በመሳሰሉ መተግበሪያዎች በኩል ሲሆን፤ የሚላከው ደግሞ ወደ ጓደኛዎት አልያም ወደ የማያውቁት ሰው ሊሆን ይችላል።


ወደ እርስዎ የሚላኩ መልዕክቶች ደግሞ ብዙ ጊዜ ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ የሚሉ ማሳሰቢያዎች ይበዟቸዋል።


5. ከበይነ መረብ የሚመጡ ድንገተኛ መልዕክቶች


ስልክዎን በመጠቀም በይነ መረብን (ኢንትርኔት) በሚያስሱበት ወቅት ወደ ሌላ ድረ-ገጽ የሚያሸጋግሩ መልዕክቶች በተደጋጋሚ የሚመጡ ከሆነ የስልክዎ መጠለፍ ነገር እውን ሊሆን ይችላል።


መልዕክቱን ሲጫኑ በአንድ ጊዜ ወደ ሁለትና ሦስት የድህ-ረገጾች አድራሻዎች የሚመራዎ ከሆነ በፍጥነት ይውጡ።


6. አጠራጣሪ መተግበሪያዎችና ገንዘብ ነክ ጥያቄዎች


አንዳንድ ጊዜ እርስዎ ያልገዙት ወይም ከበይነ መረብ ያላወረዱት መተግበሪያ ስልክዎት ላይ ሊመለከቱ ይችላሉ። ምናልባትም የሞባይል ዳታ እና የጽሁፍ መልዕክት ላይ የዋጋ ጭማሪም ሊያስተውሉ ይችላሉ።


የክሬዲት ካርድና የሞባይል ገንዘብ ማንቀሳቀሻ መንገዶችን የሚጠቀሙ ከሆነ ይህ ሁኔታ ለጠላፊዎች ምቹ አጋጣሚ ሊፈጥርላቸው ይችላልና ይጠንቀቁ።


ስለዚህ የይለፍ ቃሎችንና የግል መረጃዎችን ስልክዎት ላይ ባያስቀምጡ ይመረጣል፤ አልያም በጠላፊዎች እንዳይገኝ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል።


7. ያልተለመዱ ድምጾች


የድምጽ ጥሪ በሚያደርጉበት ወቅት ያልተለመዱና ከዚህ በፊት ያልነበሩ ድምጾች የሚሰማዎት ከሆን ምናልባት ስልክዎ የጠላፊዎች ሰላባ ሆኖ ሊሆን ይችላል። ይባስ ብሎም የስልክ ጥሪዎችዎ እየተቀዱም ሊሆን ይችላል።


🏷 መፍትሄዎች

   ━━━━━━

▫️የስልክ ማጽጃዎችን ከታማኝ ምንጭ ማግኘት


▫️እርስዎ የማያውቋቸውን መተግበሪያዎች ከስልክዎ ማጥፋት


▫️ብዙ ሰው የሚጠቀማቸው ነጻ የኢንተርኔት አገልግሎቶችን አለመጠቀም


▫️ስልክዎን በቀላሉ ሊታወቅ በማይችል የይለፍ ቃል መዝጋት


▫️ከማይታወቁ ምንጮች መተግበሪያዎችን አለመጫን


▫️ስልክዎና በስልክዎ ላይ ያሉ መተግበሪያዎችን ቶሎ ቶሎ ማሳደስ (update) 


▫️ስልክ ክፍያዎንና የዳታ አጠቃቀምዎን ይቆጣጠሩ

 DV 2023 እንዴት ራሳችን መሙላት እንችላለን?

 ዲቪ 2023 ለመሙላት መከተል ያለብንን መንገዶች እነሆ

›በመጀምሪያ ዲቪ መሙላት የምንችለዉ ከ መስከረም 27,2014 በኢትዮጵያ ወይም በፈረንጆች ኦክቶበር ሀሙስ 07/2021 ጀምሮ ህዳር  09/2021 ለሊት 6፡00 ድረስ ብቻ ነው።

DV-2023 Program: Online Registration

DV-2023 Program: The online registration period for the DV-2023 Program begins on Wednesday, October 7, 2021 at 12:00 noon, Eastern Daylight Time (EDT) (GMT-4), and concludes on Tuesday, November 09, 2021 at 12:00 noon, Eastern Standard Time (EST) (GMT-5). Individuals who submit more than one entry during the registration period will be disqualified.

DV-2023 Program Instructions

›የዲቪ ፎርሙን ከመሙላታችን በፊት ማሟላት ያሉብን ነገሮች፦

እያንዳንዱ የ DV አመልካች የትምህርት / የሥራ ልምድ ማሟላት አለበት

ማለትም

በ ፕሮግራሙ መሰረትም-

• ቢያንስ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ወይም ተመጣጣኝ, የ 12 ዓመት ትምህርት

በሚገባ ያጠናቀቀ / ያጠናቀቀች።

ወይም

• ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ የሁለት አመት የሥራ ልምድ ያለው።

•ጉርድ ፎቶ ግራፍ

በመቀጠልም

www.dvlottery.state.gov

 በሚለው ዌብ ሳይት መግባት

›ዌብ ሳይቱ ዉስጥ ገብተን Entry ሚለውን በመጫን መቀጠል

በፎቶ መልክ የተቀመጠልንን Authentication code በድጋሚ በመጻፍ ወደ

ፎርም መሙያዉ መግባት።

ፎርም አሞላል

1. Name - ስም - Last/Family Name (የመጨረሻ/የቤተሰብ ስም ወይም

የአያት ስም) ፣ Middle Name- (የመካከለኛ ስም ወይም የአባት ስም) ፣

First Name (የመጀመሪያ ስም ወይም የእርሶን ስም) በፓስፖርትዎ ላይ

ያለውን ስም ሳያሳስቱ በእንግሊዝኛ መጻፍ።

2. Gender - ፆታ - ወንድ (Male) ወይም ሴት(Female) መምረጥ።

3. Birth date - የልደት ቀን - መጀመሪያ Month (ወር) ፣ Day (ቀን) ፣ Year

( ዓመት) በፈረንጆች አቆጣጠር በተሰጠው ቦታ መጻፍ።.

4. City Where You Where Born - የተወለዱበትን ከተማ.

5. Country Where You Were Born - የተወለዱበትን ሀገር

6. Country of Eligibility for the DV Program - ለ DV መርኃ-ግብር

ብቁ የሆነ ሀገር ማለትም yes ሚለዉ ላይ በመተው ማለፍ

7. Entrant Photograph - የመግቢያ ፎቶግራፍ ማስገባት

- የቅርብ ጊዜ ጉርድ ፎቶግራፍ -ፎቶ ግራፉ በደንብ የሚታይ ልኬቱ 600ፒክስል

* በ600 ፒክስል የሆነ መጠኑ ከ 240 ኪሎባይት የማይበልጥ ከለር ፎቶ ግራፍ

፣JPEG Format መሆን አለበት።

8. Mailing Address - የፖስታ መላኪያ አድራሻ መሙላት

9. Country Where You Live Today - አሁን የምንኖርበትን ሀገር መምረጥ

10. Phone Number - ስልክ ቁጥር ማስገባት ለኢትዮጲያ +251 ብለን

በመጀመር ስልካችንን ማስገባት / አለማስገባትም ይቻላል

11. E-mail Address - የ ኢሜል አድራሻንን ማስገባት

12. What is the highest level of education you have achieved,

as of today?

የትምህርት ደረጃችንን መምረጥ

13. What is your current marital status?- በአሁን ሰአት ያለን የትዳር

ሁኔታ መምረጥ

14 . Number of Children - የልጅ ብዛት በቁጥር መጻፍ

እያንዳንዱ የተወለዱ ሕጻናት እንዲሁም የማደጎ ልጆች፣ የእንጀራ ልጆች

በእርስዎ ፎርም ውስጥ እያንዳንዱ ያላገቡ ህጻናት, ምንም እንኳን ልጅዎ

ከእርስዎ ጋር አብረው ባይኖሩም መሞላት አለባቸዉ።

»በመጨረሻም continue በማለት Confirmation Number ያለበትን

ወረቀት ፕሪንት በማድረግ ማስቀመጥ እና በ Confirmation Number ን

DV-2023 ሲወጣ ማየት እንችላለን።

DV-2023 Submission Confirmation : Entry success

በዚ መሰረት ፎርሙን በመሙላት እድላችሁን መሞከር ትችላላችሁ ፔጃችንም

መልካም እድል ይመኝላቹሀል

ይሄን መረጃ ለወዳጆ ሼር በማድረግ ማስተላለፍ ትችላላችሁ

Congratulation

 ክቡር አቶ ደምስ ገብሬ የጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ ሆነው  በመሰየሞ የደቡብ ሶዶ ወረዳ የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት ማኔጅመንት አካላትና ባለሙያዎች  የተሰማቸውን ደስታ እየገለፁ መልካም የሥራ ዘመን እንዲሆንልዎ ከልብ እንመኛለን!!!



የደቡብ ሶዶ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት

  መግቢያ የወረዳው ሳይንስናኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ / ቤት የተቋቋመበት ዋናው ምክንያት በወረዳው የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በማልማትና በሁሉም ስፍራ በስፋት በመጠቀም የህብረተሰቡን ኑ...