
የአይፎን 13 የሳተላይት ግንኙነቶችን እንደ አማራጭ ይዞ እንደሚመጣ ተነገረ፡፡
በመስከረም ወር ለገበያ እንደሚቀርብ የሚጠበቀው አዲሱ የአፕል ኩባንያ ምርት አይፎን 13 የሳተላይት ግንኙነቶችን እንደ አማራጭ ይዞ እንደሚመጣ ተነገረ፡፡
የቴሌኮም አገልግሎቶች ተደራሽ በማይሆኑባቸው አካባቢዎች በታችኛው የመሬት ምሕዋር የሚገኙ ሳተላይቶችን በመጠቀም የድምፅ እና የአጭር መልዕክት አገልግሎቶችን ተደራሽ ማድረግ እንደሚችል ሲኔት ዘግቧል፡፡
አዲሱ ስልክ በሳተላይት አማካኝነት አገልግሎት መስጠት የሚያስችለው Qualcomm X60 የተባለ ቺፕ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ይህ አዲስ ገፅታ ከቴሌኮም አገልግሎቶች ርቀው ለሚኖሩ እና መሰል አገልግሎቶች ተደራሽ ባልሆኑባቸው አካባቢዎች የሚጓዙ ተጠቃሚዎችን ትኩረት እንደሚያገኝ ይጠበቃል፡፡ (Cnet, AICE)
No comments:
Post a Comment