ቀን 21/08/2014 ዓ.ም በጉራጌ ዞን በደቡብ ሶዶ ወረዳ ለመጀመሪያ ጊዜ በወረዳ ማዕከል ደረጃ የፈጠራ ሥራዎች ውድድርና ኤግዚቢሽን እንዲሁም የፓናል ውይይት በደማቅ ሁኔታ መካሄዱን የደቡብ ሶዶ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት አስታወቀ።

 በቀን 21/08/2014 ዓ.ም ማለትም በዕለተ አርብ በወረዳው በሚገኙ ሁለት ፅ/ቤቶች እነኚህም የደቡብ ሶዶ ወረዳ ት/ቤቶች ፅ/ቤት እና የደቡብ ሶዶ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት በጋራ በመሆን በወረዳው ለመጀመሪያ ጊዜ በወረዳ ማዕከል ደረጃ የሳይንስ ፈጠራና የሒሳብ ሥራዎች ውድድርና የፓናል ውይይት “ሥራ ፈጣሪ እንጂ ሥራ ፈላጊ ትውልድ አንፈጥርም” በሚል መሪህ ቃል በደማቅ ሁኔታ በዛሬው ዕለት ተከበረ። 

የመርሐ ግብሩ ሂደት በመጀመሪያ በዕለቱ በወረዳው በሚገኙ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቶችና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ተመርጠው የመጡ የፈጠራ ሥራዎች በወረዳው ዋና አስተዳዳሪና በአስተባባሪው መሪነት ጉብኝት በማድረግ የዕለቱ መርሐ ግብር በይፋ መጀመሩን በማብሰር የተጀመረ ሲሆን ቀጥሎም ከጉብኝቱ በኋላ የመግቢያ ንግግር በሁለቱ ፅ/ቤቶች ኃላፊዎች አማካኝነት የተደረገ ሲሆን በመቀጠልም በወረዳው ዋና አስተዳዳሪ የመክፈቻ ንግግር በማድረግ ቀጥታ ወደ ፓናል ውይይቱ ተገብቷል።

የፓናል ውይይቱ በወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሠለ ጫካ ፣ የደ/ሶ/ወ/ት/ቤቶች ፅ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ታደለ ብርሃኔ እንዲሁም የደ/ሶ/ወ/ሳ/ኢ/ቴ/ፅ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ደግሞ አቶ ደመላሽ ውዴ በጋራ በመሆን የመሩት ሲሆን በውይይቱ ላይ እጅግ ገንቢና ጠንካራ የሆኑ ሐሳቦች ከውይይቱ ተሳታፊዎች የተነሳ ሲሆን በቀጣይም ወረዳችንን አልፎ ዞናችንን እንዲሁም ሀገራችንን ወደ ተሻለ የኢኮኖሚ ዕድገት የሚያሸጋግሩ የፈጠራ ሥራዎች እንደሚሰሩም ዛሬ የተደረገው የፈጠራ ውድድር አመላካች እንደሆነ ከመድረኩም እንዲሁም ከተሳታፊው አመላክተዋል። 

ከተሳታፊዎች መካከል ከቡኢ ኢንደስትሪያል ኮሌጅ ምክትል ዲን የሆኑት አቶ ደረጄ እና ከጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ አቶ ታሪኩ በውይይቱ ላይ ጠንካራ ሀሳብ የሰጡ ሲሆን በተጨማሪም በወላጅ ዘርፍ አቶ አበራ ሃይሌ ሀሳባቸውን በተገቢው መልኩ ያንፀባረቁ ሲሆን ወደ መጨረሻው መርሐ ግብር ከመኬዱ በፊት የቡኢ ኢንደስትሪያል ኮሌጅ ዋና ዲን የሆኑት አቶ ሙሉጌታ ለአጭር ደቂቃ የኮሌጁ ኃላፍትና እንዲሁም የሚሰጣቸው አገልግሎቶችን በመጥቀስ ይህንን የፈጠራ ሥራዎችን በሚገባ እንደሚያግዝ በማውሳት ንግግራቸውን ቋጭተዋል።  

በመጨረሻም በፈጠራ ሥራዎች ውድድር በዕለቱ ጥሩ የፈጠራ ሥራዎችን ላሳዩ ት/ቤቶች እንዲሁም ተማሪዎች የማበረታቻና የዕውቅና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል። የዕውቅናው ሰርትፊኬትና የማበረታቻ ሽልማት በሦስት ዘርፍ ከአንድ እስከ ሦስት ደረጃ ለወጡት የተበረከተላቸው ሲሆን፦ 

ይህም የመጀመሪያው በክላስተር ደረጃ፦  1ኛ ጎጌቲ ክላስተር 3000 ብር ተሸላሚ 

                                             2ኛ ጎሴ ሳለን ክላስተር 2000 ብር ተሸላሚ

                                             3ኛ ጎጌቲ ክላስተር 1000 ብር ተሸላሚ

የሁለተኛው በት/ቤቶች ደረጃ፦ 1ኛ ጎጌቲ 3 የመ/ደ/ት/ቤት 3000 ብር ተሸላሚ

                                  2ኛ ኬላ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት 2000 ብር ተሸላሚ

                                  3ኛ አጋምሰናዶ የመ/ደ/ት/ቤት 1000 ብር ተሸላሚ

የሦስተኛው በተማሪዎች ደረጃ፦ 1ኛ ተማሪ ቢሊሊኝ ይብሳ 3000 ብር ተሸላሚ

                                   2ኛ ተማሪ አላምረው ይፋ 2000 ብር ተሸላሚ

                                   3ኛ ተማሪ ሙሉቀን አበራ 1000 ብር ተሸላሚ ሲሆኑ 

የአራተኛው ዘርፍ በፈጠራው ላይ ለተሳተፉ ሁሉ በክላስተር፣ በተማሪ፣ በት/ቤቶች የተሳትፎ የዕውቅና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል።

በቀጣይ ከዚህ በላቀና በጠነከረ የፈጠራ ሥራዎች ላይ ውድድር እንደሚደረግ በማሳሰብ ይህ ጅምር እንጂ ፍፃሜ እንዳይደለ በመድረኩ ለተማሪዎች እንዲሁም ለመምህራን በማሳሰብ የዕለቱን መርሐ ግብር ተጠናቋል።

የዘመነ ዲጂታል ኢኮኖሚ የዕድገታችን መሠረት ነው!!!

@SSWSIT















ቀን 04/08/2014 ዓ.ም ሁለተኛው ዙር የፈጠራ ሥራዎች ኤግዚቢሽን በጉራጌ ዞን በደቡብ ሶዶ ወረዳ በክላስተር ደረጃ መከበሩን የደቡብ ሶዶ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት አስታወቀ።

                                

በቀን 04/08/2014 ዓ.ም ማለትም በዕለተ ማክሰኞ በሁለት የት/ት ክላስተሮች የሳይንስና ፈጠራ ሥራዎች ኤግዚቢሽን ተከበረ፤ ኬላ ክላስተር የአንደኛው ክላስተር ስም ሲሆን በዚህም ክላስተር አራት ት/ቤቶችን በሥሩ የሚይዝ ሲሆን በዛሬው ዕለት የክላስተሩ ሱፐርቫይዘር የሆኑት መ/ር ዘነበ ጀማል ኤግዝቢሽኑን ለመሳተፍ የመጡ መምህራንና ተማሪዎችን የእንኳን ደህና መጣችሁ!!! እና የኤግዚቢሽኑን ዓላማና ግብ በተጨማሪም መልዕክቶችን በማስተላለፍ የኤግዚቢሽኑ መጀመር በይፋ አብስረው መርሐ ግብሩን ያስጀመሩ ሲሆን በዚህ ክላስተር ላይ ከተለያዩ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቶች የመጡት ተማሪዎች የሰሯቸውን የፈጠራ ሥራዎች እንዲያብራሩና እንዲያስጎበኙ ተደርገው በዚህ ክላስተር ላይ እስከ 19 የሚሆኑ የፈጠራ ሥራዎች ታይተዋል።

በመርሐ ግብሩ መጨረሻ አካባቢ ከተሳታፊዎች የኤግዚቢሽኑ ቆይታና የሚሰጣቸው አስተያየት ካለ ብለው የመድረኩ አስተባባሪና የክላስተሩ ሱፐርቫይዘር የሆኑት መ/ር ዘነበ ጀማል ዕድል የሰጡ ሲሆን ከኤግዚቢሽኑ ተሳታፊዎች ጠንካራና ገንቢ ሀሳቦችን ተነስተው፤ እንደ ጥያቄ የተነሱ ሀሳቦችን ደግሞ ከወረዳው ት/ቤቶች ፅ/ቤት የመምህራንና የት/ት አመራር ልማት ቡድን መሪ የሆኑት አቶ አውግቾ ከበደ እንዲሁም የወረዳው ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት ባለሙያዎች አቶ ሀብታሙ ባልቻ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ሥራዎች ክትትልና ድጋፍ አቅም ግንባታ ሥራ ሂደት አስተባባሪ እና አቶ ናትናኤል ይልማሽዋ የኢኮቴ መሠረተ ልማት ዝርጋታና አስተዳደር ሥራ ሂደት አስተባባሪ በተነሱት ሀሳቦችና ጥያቄዎች በተገቢው ሥልጠና በሚመስል መልኩ በማብራራት ሰፊ ትንተና ሰጥተዋል። በመጨረሻም ይህ ኤግዚቢሽን ቀጣይነት እንዳለው ከመድረኩ በማውሳት የዕለቱ መርሐ ግብር ተጠናቋል።

ሌላኛው ክላስተር ደግሞ ኬላ 2ተኛ ክላስተር የሚባል ሲሆን በዚህ ክላስተር ሦስት ት/ቤቶች የሚይዝ ሲሆን ነገር ግን አንደኛው ት/ቤት ገና በጅምር ላይ ያለ በመሆኑ በዚህ ክላስተር ተሳታፊዎች ሁለት ት/ቤቶች ነበሩ እነዚህም ኬላ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤትና ዳሙ ገነት ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ናቸው። በዚህ መርሐ ግብር ላይ የክላስተሩ ሱፐርቫይዘር የሆኑት መ/ር መለሰ ፋንታዬና የኑረና ኬላ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ርዕሰ መ/ር የሆኑት መ/ር ሻውል ወርቁ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የኤግዚቢሽኑ መጀመር በይፋ በማብሰር በኤግዚቢሽኑ ላይ በፈጠራ ሥራዎች ላይ ለመሳተፍ የመጡ ተማሪዎችን የሰሯቸውን የፈጠራ ሥራዎች እንዲያብራሩና እንዲያስጎበኙ አድርገዋል። በማኅበረሰቡ ዘንድ ያሉትን ችግሮች የሚፈቱ የፈጠራ ሥራዎች እስከ 18 የሚያህሉ በዚህ ክላስተር ላይ የታዩ ሲሆን በጉብኝት ወቅት በቀረቡት የፈጠራ ሥራዎች ላይ ግብዓት (ማሻሻያ) የሚሆኑ ሀሳቦችን የወረዳው ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ደመላሽ ውዴ ለተማሪዎቹ በመስጠት ጉብኝቱ ላይ እጅግ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል። በመጨረሻም በተሳታፊዎች ለቀረበላቸው ጥያቄና የግብዓት ሀሳቦች ላይ በመጀመሪያ የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት ባለሙያዎች የሆኑት አቶ ሀብታሙ ባልቻና አቶ ናትናኤል ይልማሽዋ በመቀጠልም የወረዳው ት/ቤቶች ፅ/ቤት ባለሙያ የሆኑት አቶ አውግቾ ከበደ ለቀረቡት ሀሳቦች ምላሽ የሰጡ ሲሆን የመርሐ ግብሩ አጠቃላይ ሁኔታዎች ላይ እንዲሁም በቀረቡ ሀሳቦች ላይ በአፅንዖት ምላሽ የሰጡት የወረዳው ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ደመላሽ ውዴ ሲሆኑ በኤግዚቢሽኑ በነበራቸው ቆይታ ድስተኛ እንደ ነበሩና ተሳታፊዎቹ ያነሷቿቸው ሀሳቦች እጅግ ገንቢና ተገቢ መሆኑን በማውሳት አክለውም ከዚህ ቀደም ማነቆ በነበሩት ችግሮች ምክንያት በርካታ ሥራዎች ሊሰሩ አለመቻላቸው ነገር ግን ከዚህ በኋላ ከባለድርሻ አካላት ትኩረት በመስጠት በጋራ የምንሰራው ጉዳይ ነው ሲሉ በመግለፅ እንዲሁም በርካታ ግንዛቤዎችን በማስጨበጥ መርሐ ግብሩ ተጠናቋል።










የደቡብ ሶዶ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት

  መግቢያ የወረዳው ሳይንስናኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ / ቤት የተቋቋመበት ዋናው ምክንያት በወረዳው የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በማልማትና በሁሉም ስፍራ በስፋት በመጠቀም የህብረተሰቡን ኑ...