የአይፎን 13 የሳተላይት ግንኙነቶችን እንደ አማራጭ ይዞ እንደሚመጣ ተነገረ፡፡


 

የአይፎን 13 የሳተላይት ግንኙነቶችን እንደ አማራጭ ይዞ እንደሚመጣ ተነገረ፡፡

በመስከረም ወር ለገበያ እንደሚቀርብ የሚጠበቀው አዲሱ የአፕል ኩባንያ ምርት አይፎን 13 የሳተላይት ግንኙነቶችን እንደ አማራጭ ይዞ እንደሚመጣ ተነገረ፡፡

የቴሌኮም አገልግሎቶች ተደራሽ በማይሆኑባቸው አካባቢዎች በታችኛው የመሬት ምሕዋር የሚገኙ ሳተላይቶችን በመጠቀም የድምፅ እና የአጭር መልዕክት አገልግሎቶችን ተደራሽ ማድረግ እንደሚችል ሲኔት ዘግቧል፡፡

አዲሱ ስልክ በሳተላይት አማካኝነት አገልግሎት መስጠት የሚያስችለው Qualcomm X60 የተባለ ቺፕ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ይህ አዲስ ገፅታ ከቴሌኮም አገልግሎቶች ርቀው ለሚኖሩ እና መሰል አገልግሎቶች ተደራሽ ባልሆኑባቸው አካባቢዎች የሚጓዙ ተጠቃሚዎችን ትኩረት እንደሚያገኝ ይጠበቃል፡፡ (Cnet, AICE)

 


🚩 YouTube የDislike Buttonኑን ከPublic እይታ ወደ Private ሊቀይር ነው ይሄም ማለት YouTube ላይ የሚለቀቅ ማንኛውንም Video ተመልካቹ ወይም አንድ ግለሰብ Dislike ቢያደርግ የዛን የDislike መጠን ሌሎች ሰዎች ማየት አይችሉም ለChannleሉ ባለቤት ብቻ ይታያል ማለት ነው.. YouTube ይሄንን ያደረገበት ምክንያት (Dislike Attackን) ለመከላከል ነው Dislike Attack ማለት አንዳንድ ሰዎች በግልም በGroupፕም በመሆን ሆን ብለው አንዳንድ የYouTube Channelሎችን ኢላማ   በማድረግ እዛ Channle ላይ የሚለቀቁትን Video Dislike ያደርጋሉ ይሄ ደግሞ የChannel Creatorች ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ በመሆኑ ነው።

የደቡብ ሶዶ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት

  መግቢያ የወረዳው ሳይንስናኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ / ቤት የተቋቋመበት ዋናው ምክንያት በወረዳው የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በማልማትና በሁሉም ስፍራ በስፋት በመጠቀም የህብረተሰቡን ኑ...