✳️ ሰዎች የሚሰበሰቡባቸው ሥፍራዎችን ደህንነት ለማስጠበቅ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ጥቅም ላይ እየዋለ ነው፡፡


🚩መቀመጫውን በሀገረ አሜሪካ ማሳቹሴትስ ያደረገው ኢቮልቭ የተባለ የቴክኖሎጂ ተቋም ትምህርት ቤቶች፣ ስቴዲየሞች እና ሰዎች በብዛት የሚገኙባቸውን  መሰል ሥፍራዎች ደህንነት ለማስጠበቅ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን ጥቅም ላይ አውሏል፡፡ 


🚩በእነዚህ ሥፍራዎች ለመገልገል የሚመጡ ሰዎች በተለመደው የፍተሻ አይነት ማለፍ አይጠበቅባቸውም፡፡ ይልቁንም በግራ እና ቀኝ በቆሙ ሁለት ሰሌዳዎች መካከል ያለምንም ንክኪ፣ ሰልፍ እና እንግልት በማለፍ ይስተናገዳሉ፡፡


🚩ቴክኖሎጂው የሚሰራው እጅግ የተራቀቁ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መጠቆሚያዎችን (ሴንሰር) ከካሜራዎች ጋር በማቀናጀት እንደሆነ ፎክስ ኒውስ ዘግቧል፡፡ 


🚩በዚህም ምንም አይነት ጉዳት የሌላቸውን ብረት ነክ ቁሳቁሶች ከሽጉጥ፣ ከስለት እና ተቀጣጣይ መሣሪያዎች በመለየት ለሚመለከታቸው አካላት አስቸኳይ የማንቂያ መልዕክት ይልካል፡፡  


🚩ይህም በብዙ ሥፍራዎች የሚገኙትን የብረት ነክ ቁሳቁሶችን በአጠቃላይ እንደ አደገኛ መሣሪያ በመቁጠር የፍተሻ አገልግሎት ከሚሰጡ መሣሪያዎች በእጅጉ እንዲለይ አስችሎታል፡፡ 


🚩ተቋሙ ከአውሮፓውያኑ 2019 ጀምሮ በስፖርት ውድድር መታደሚያ ሥፍራዎች፣ ሆስፒታሎች፣ ትምህርት ቤቶች እና መሰል ስፍራዎች ቴክኖሎጂውን ተግባራዊ በማድረግ ሦስት መቶ ሚሊዮን ሰዎች መፈተሸ መቻሉን አስታውቋል፡፡                                  @SSWSIT

'image.png' failed to upload.
Uploading: 131000 of 280117 bytes uploaded.
Uploading: 32750 of 207588 bytes uploaded.






No comments:

Post a Comment

የደቡብ ሶዶ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት

  መግቢያ የወረዳው ሳይንስናኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ / ቤት የተቋቋመበት ዋናው ምክንያት በወረዳው የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በማልማትና በሁሉም ስፍራ በስፋት በመጠቀም የህብረተሰቡን ኑ...