🚩የጃፓኑ መኪና አምራች ቶዮታ ኩባንያ የሰዎችን በጨረቃ ላይ የመኖር እቅድ ሊያሳካ ይችላል የተባለለት መኪና ሊያመርት መሆኑን አስታወቀ፡፡
🚩ከጃፓኑ የሕዋ ተቋም ጋር በጥምረት ወደ ስራ የገባው ቶዮታ ኩባንያ መኪናውን በአውሮፓውያኑ 2020ዎቹ መጨረሻ ወደ ጨረቃ የመላክ እቅድ እንዳለው ዴይሊ ሜይል አስነብቧል፡፡
🚩ሉናር ክሩዘር የሚል መጠሪያ የተሰጠው መኪና ሁለት ሰዎችን የመያዝ አቅም ሲኖረው በጨረቃ ላይ ለአስራ አራት ቀናት ያህል ከቦታ ቦታ እየተንቀሳቀሱ ለመስራት እና በውስጡ ለመኖር ያስችላል፡፡
🚩ተሽከርካሪው በሚኖረው የሮቦት እጅ አማካኝነት የተለያዩ ምርመራዎችን እና ጥገናዎችን ማከናውን እንደሚችል ይጠበቃል፡፡ የሮቦት እጁ ከባድ ነገሮችን ለማንሳት እና የተለያዩ መሣሪያዎችን ለመያዝ እንዲያገለግል ጫፉን መቀያየር የሚቻል መሆኑ ተመላክቷል፡፡
🚩የሰው ልጅ በጨረቃ እና በሌሎችም የሕዋ አካላት ላይ ለሚያደርገው የጥናት እና ምርምር እንዲሁም በቀጣይ ለመኖሪያ አማራጭ ፍለጋው መኪናው እገዛ እንደሚያደረግ ይጠበቃል፡፡
No comments:
Post a Comment