☞በአለማችን ይኖራሉ ብለው የማይገምቷቸው አስገራሚ ድረ ገፆች




✔️✔️✔️✔️✔️✔️✔️✔️✔️✔️✔️


☞ በአሁኑ ወቅት መጠኑ ይለያይ እንጂ አንዳንዶቻችን በየቀኑ የኢንተርኔት መረቦችን መቃኘታችን የተለመደ ተግባር ሆኗል።


የምንቃኛቸው ድረ ገፆችም ብዙ ጊዜ የምናውቃቸውን አልያም በጣም ታዋቂዎቹን ነው።


አንዳንድ ጊዜም በፌስቡክ አማካኝነት ያገኘናቸው መረጃዎች አዳዲስ ድረ ገፆችን ያስተዋውቁናል።


እነዚህን አዳዲስ ድረ ገፆችም ጠቃሚ ሆነው ስናገኛቸው ለሌላ ጊዜ እንድንጠቀማቸው ቡክማርክ አድረገን እናስቀምጣቸዋለን።


ከዚህ በታች የተዘረዘሩት 9 ድረ ገፆች ግን ምናልባትም አይተናቸው የማናውቃቸው እና የተለየ አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው ይላል ቴክወርም የተሰኘው የቴክኖሎጂ ድረ ገፅ ዘገባ።


1. 10Minutemail.com


ይህ ድረ ገፅ ለ10 ደቂቃ የሚቆይ የኢሜል አድራሻ ለመክፈት ያስችላል።


ድረ ገፁ የተላላክናቸውን መልዕክቶች እና የኢሜል አድራሻውን ከ10 ደቂቃዎች በኋላ ሙሉ በሙሉ ያጠፋዋል።


10Minutemail.com እንደከፈትነው ምንም ምዝገባ ሳያስፈልገን ራሱ የኢሜል አድራሻ ይሰጠናል።

👇👇👇👇

በተጨማሪም Tempmail ለዚህ ይጠቅመናል አጠራጣሪ ድረገጾች ስንከፍት ኢሜል ሲጠይቁን በዚህ መጠቀም እንችላለን


2. የሀሰት ስም እና አድራሻ ፈጣሪ - Fake Name Generator


በጣም አይነአፋር የሆኑ፣ የግል ጉዳያቸው የሚያስጨንቃቸው እና ትክክለኛ ስማቸውን ይፋ ማድረግ የማይፈልጉ ሰዎች በዚህ ድረ ገፅ አማካኝነት የሀሰት ስም እና ዝርዝር መረጃዎችን መፍጠር ይችላሉ።


Fakenamegenerator.com  


3. አንዳንድ ድረ ገፆች የማይከፍቱት እንዳልከፍታቸው ስለታገድኩ ነው ወይስ ስለማይሰሩ? - Down for Everyone or Just Me


አንዳንድ ጊዜ ኮምፒውተርዎ የተወሰኑ ድረ ገፆችን አልከፍት ሊልዎት ይችላል። እናም በዚህ ድረ ገፅ አማካኝነት እውን ይህ ድረ ገፅ አልከፍት ያለዎት ስለማይሰራ ነው አልያስ ሆን ተብሎ እንዳይከፍቱት ስለተደረገ ነው የሚለውን ማረጋገጥ ይችላሉ።


Downforeveryoneorjustme.com 


4. የቀናት ልዩነትን ለማስላት - Date and Time 


በዚህ ድረ ገፅ ደግሞ በቀናት እና አመታት መካከል ያሉ ልዩነቶችን ለማስላት ይጠቅማል።


ለአብነትም እድሜያችን በቀናት ለማስላት የተወለድንበትን ቀን፣ ወር እና አመት እና የእለቱን ቀን ወር እና አመት በማስገባት በምድር ላይ ለስንት ቀናት ቆይታ እንዳደረግን ማስላት እንችላለን።


የምናሰላው ቀን በአላትን እና ቅዳሜ እና እሁድን አካቶ አልያም ሳያካትት ስንት እንደሆነም ማወቅ ያስችላል።


timeanddate.com 


5. የድረ ገፆችን የፊት ገፅ ምስል ለማስቀረት - Web Capture


የተለያዩ ድረ ገፆችን የፊት ገፅታ ምስል ለማስቀረት እና ወደ JPG/JPEG፣ PNG አልያም PDF ፎርማት ለመቀየር ይህን ድረ ገፅ ይጠቀሙ። 


webcapture.net/  


6. ጎግልን ያለምንም የሀገር ገደብ ለመጠቀም - Google NCR


የጎግል ድረ ገፅን (google.com) ስንከፍት ጎግል ወደየሀገራችን ዶሜን ያስገባናል። ለምሳሌ ጎግልን በኢትዮጵያ ስንከፍት google.com.et ወደሚለው ያሸጋግረናል። ይህም የሚሆነው ጎግል እንደየሀገራቱ የሚከለክለው እና የሚፈቅደው ስላለው ነው።


እናም ጎግልን ያለምንም የሀገራት ገደብ ለመክፈት google.com/ncr ብለን መፈለግ በቂ ነው።


7. የተላኩልን ፋይሎች በቫይረስ የተጠቁ መሆን አለመሆናቸውን ለማረጋገጥ -የተላከልን Virustotal


ከጓደኞቻችን አልያም ከማናውቀው ግለሰብ የሚያጠራጥር ፋይል ከተላከልን እና ከኢንተርነየት በቀጥታ ካወረድነው በዚህ ድረ ገፅ አማካኝነት  ፋይል ቫይረስ መያዙን እና አለመያዙን ማወቅ እንችላለን።


ቪሩስቶታል ነፃ የኢንተርኔት የቫይረስ መመርመሪያ (ስካነር) ነው።


8. በአለማችን እየተከናወኑ ያሉ ወቅታዊ የመረጃ ዘረፋዎችን የሚያሳይ ካርታ - IPviking


በአለም ዙሪያ እየተከናወኑ ያሉ የመረጃ ምንተፋዎች፣ የአይፒ አድራሻዎች፣ የመረጃ ዘራፊዎቹን አድራሻ እና የመሳሰሉ መረጃዎችን http://map.norsecorp.com/#/ በተባለው ድረ ገፅ ላይ መመልከት ይቻላል።


9. Hackertyper


ይህን ድረ ገፅ ከፍተን የተለያዩ ፊደላትን እና ቁጥሮችን ስንጫን መረጃ ዘራፊዎች የሚጠቀሙበትን አይነት ገፅ ይከፍትልናል።


በዚህም ጓደኞቻችን እና ወዳጆቻችን የተለያዩ ድርጅቶችን መረጃዎችን እየሰረቅን ለማስመሰልና ለመሸወድ እንችላለን።


http://hackertyper.net/


10. Password Generator 


ጠንካራ  እና በቀላሉ ብሬክ የማይደረግ የይለፍ ቃል ለፌስቡክ ለኢሜል ለሌሎች ፓስወርድ ለሚጠይቁ በሙሉ ጠንካራ የይለፍ ቃል (ፓስወርድ)  ለመመስረት

 📲 ስልክዎ እንደተጠለፈ የሚያሳዩ ሰባት ምልክቶች

 ▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃


1. የስልክዎ ፍጥነት ከቀነሰ


ተንቀሳቃሽ ስልክዎ ከሌላው ጊዜ በተለየ ትዕዛዞችን ለማከናወን ረዘም ያለ ጊዜ የሚፈጅ ከሆነ፤ ባዕድ ሶፍትዌሮች (ማልዌር) እያስቸገሩት ነው ማለት ነው።


እነዚህ ማልዌር የተባሉት ቫይረሶች ዋነኛ ሥራቸው የስልክዎን አጠቃላይ እንቅስቃሴ ማዘግየት ሊሆን ስለሚችል፤ በአፋጣኝ ማስወገድ ተገቢ ነው።


2. ስልክዎ በጣም የሚግል ከሆነ


ስልክዎት ከተለመደው ከፍ ባለ ሁኔታ የሚግል ከሆነ፤ ችግር አለ ማለት ነው። በፍጥነት እርምጃ ይውሰዱ አልያም ባለሙያ ያማክሩ።


3. የስልክዎ የባትሪ ኃይል ቶሎ የሚያልቅ ከሆነ


ስልክዎ ከፍተኛ ሙቀት አለው ማለት ደግሞ የባትሪው ኃይል ቶሎ ቶሎ ያልቃል ማለት ነው።


ምናልባት ስልክዎ አዳዲስ መተግበሪያዎችንና ሶፍትዌሮችን ለማደስ በሚሞክርበት ወቅት የባትሪውን ኃይል ሊጨርስ ይችላል። ነገር ግን ምክንያቱ ይህ ካልሆነ ስልክዎ ተጠልፎ ሊሆን እንደሚችል ማሰብ አለብዎ።


4. ወደ ማያውቁት ሰው መልዕክት ከተላከ ወይም ከማያውቁት ሰው መልዕክት ከደረስዎ


ብዙ ጊዜ እርስዎ የማያውቋቸው መልእክቶች የሚላኩት በዋትሳፕና በመሳሰሉ መተግበሪያዎች በኩል ሲሆን፤ የሚላከው ደግሞ ወደ ጓደኛዎት አልያም ወደ የማያውቁት ሰው ሊሆን ይችላል።


ወደ እርስዎ የሚላኩ መልዕክቶች ደግሞ ብዙ ጊዜ ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ የሚሉ ማሳሰቢያዎች ይበዟቸዋል።


5. ከበይነ መረብ የሚመጡ ድንገተኛ መልዕክቶች


ስልክዎን በመጠቀም በይነ መረብን (ኢንትርኔት) በሚያስሱበት ወቅት ወደ ሌላ ድረ-ገጽ የሚያሸጋግሩ መልዕክቶች በተደጋጋሚ የሚመጡ ከሆነ የስልክዎ መጠለፍ ነገር እውን ሊሆን ይችላል።


መልዕክቱን ሲጫኑ በአንድ ጊዜ ወደ ሁለትና ሦስት የድህ-ረገጾች አድራሻዎች የሚመራዎ ከሆነ በፍጥነት ይውጡ።


6. አጠራጣሪ መተግበሪያዎችና ገንዘብ ነክ ጥያቄዎች


አንዳንድ ጊዜ እርስዎ ያልገዙት ወይም ከበይነ መረብ ያላወረዱት መተግበሪያ ስልክዎት ላይ ሊመለከቱ ይችላሉ። ምናልባትም የሞባይል ዳታ እና የጽሁፍ መልዕክት ላይ የዋጋ ጭማሪም ሊያስተውሉ ይችላሉ።


የክሬዲት ካርድና የሞባይል ገንዘብ ማንቀሳቀሻ መንገዶችን የሚጠቀሙ ከሆነ ይህ ሁኔታ ለጠላፊዎች ምቹ አጋጣሚ ሊፈጥርላቸው ይችላልና ይጠንቀቁ።


ስለዚህ የይለፍ ቃሎችንና የግል መረጃዎችን ስልክዎት ላይ ባያስቀምጡ ይመረጣል፤ አልያም በጠላፊዎች እንዳይገኝ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል።


7. ያልተለመዱ ድምጾች


የድምጽ ጥሪ በሚያደርጉበት ወቅት ያልተለመዱና ከዚህ በፊት ያልነበሩ ድምጾች የሚሰማዎት ከሆን ምናልባት ስልክዎ የጠላፊዎች ሰላባ ሆኖ ሊሆን ይችላል። ይባስ ብሎም የስልክ ጥሪዎችዎ እየተቀዱም ሊሆን ይችላል።


🏷 መፍትሄዎች

   ━━━━━━

▫️የስልክ ማጽጃዎችን ከታማኝ ምንጭ ማግኘት


▫️እርስዎ የማያውቋቸውን መተግበሪያዎች ከስልክዎ ማጥፋት


▫️ብዙ ሰው የሚጠቀማቸው ነጻ የኢንተርኔት አገልግሎቶችን አለመጠቀም


▫️ስልክዎን በቀላሉ ሊታወቅ በማይችል የይለፍ ቃል መዝጋት


▫️ከማይታወቁ ምንጮች መተግበሪያዎችን አለመጫን


▫️ስልክዎና በስልክዎ ላይ ያሉ መተግበሪያዎችን ቶሎ ቶሎ ማሳደስ (update) 


▫️ስልክ ክፍያዎንና የዳታ አጠቃቀምዎን ይቆጣጠሩ

 DV 2023 እንዴት ራሳችን መሙላት እንችላለን?

 ዲቪ 2023 ለመሙላት መከተል ያለብንን መንገዶች እነሆ

›በመጀምሪያ ዲቪ መሙላት የምንችለዉ ከ መስከረም 27,2014 በኢትዮጵያ ወይም በፈረንጆች ኦክቶበር ሀሙስ 07/2021 ጀምሮ ህዳር  09/2021 ለሊት 6፡00 ድረስ ብቻ ነው።

DV-2023 Program: Online Registration

DV-2023 Program: The online registration period for the DV-2023 Program begins on Wednesday, October 7, 2021 at 12:00 noon, Eastern Daylight Time (EDT) (GMT-4), and concludes on Tuesday, November 09, 2021 at 12:00 noon, Eastern Standard Time (EST) (GMT-5). Individuals who submit more than one entry during the registration period will be disqualified.

DV-2023 Program Instructions

›የዲቪ ፎርሙን ከመሙላታችን በፊት ማሟላት ያሉብን ነገሮች፦

እያንዳንዱ የ DV አመልካች የትምህርት / የሥራ ልምድ ማሟላት አለበት

ማለትም

በ ፕሮግራሙ መሰረትም-

• ቢያንስ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ወይም ተመጣጣኝ, የ 12 ዓመት ትምህርት

በሚገባ ያጠናቀቀ / ያጠናቀቀች።

ወይም

• ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ የሁለት አመት የሥራ ልምድ ያለው።

•ጉርድ ፎቶ ግራፍ

በመቀጠልም

www.dvlottery.state.gov

 በሚለው ዌብ ሳይት መግባት

›ዌብ ሳይቱ ዉስጥ ገብተን Entry ሚለውን በመጫን መቀጠል

በፎቶ መልክ የተቀመጠልንን Authentication code በድጋሚ በመጻፍ ወደ

ፎርም መሙያዉ መግባት።

ፎርም አሞላል

1. Name - ስም - Last/Family Name (የመጨረሻ/የቤተሰብ ስም ወይም

የአያት ስም) ፣ Middle Name- (የመካከለኛ ስም ወይም የአባት ስም) ፣

First Name (የመጀመሪያ ስም ወይም የእርሶን ስም) በፓስፖርትዎ ላይ

ያለውን ስም ሳያሳስቱ በእንግሊዝኛ መጻፍ።

2. Gender - ፆታ - ወንድ (Male) ወይም ሴት(Female) መምረጥ።

3. Birth date - የልደት ቀን - መጀመሪያ Month (ወር) ፣ Day (ቀን) ፣ Year

( ዓመት) በፈረንጆች አቆጣጠር በተሰጠው ቦታ መጻፍ።.

4. City Where You Where Born - የተወለዱበትን ከተማ.

5. Country Where You Were Born - የተወለዱበትን ሀገር

6. Country of Eligibility for the DV Program - ለ DV መርኃ-ግብር

ብቁ የሆነ ሀገር ማለትም yes ሚለዉ ላይ በመተው ማለፍ

7. Entrant Photograph - የመግቢያ ፎቶግራፍ ማስገባት

- የቅርብ ጊዜ ጉርድ ፎቶግራፍ -ፎቶ ግራፉ በደንብ የሚታይ ልኬቱ 600ፒክስል

* በ600 ፒክስል የሆነ መጠኑ ከ 240 ኪሎባይት የማይበልጥ ከለር ፎቶ ግራፍ

፣JPEG Format መሆን አለበት።

8. Mailing Address - የፖስታ መላኪያ አድራሻ መሙላት

9. Country Where You Live Today - አሁን የምንኖርበትን ሀገር መምረጥ

10. Phone Number - ስልክ ቁጥር ማስገባት ለኢትዮጲያ +251 ብለን

በመጀመር ስልካችንን ማስገባት / አለማስገባትም ይቻላል

11. E-mail Address - የ ኢሜል አድራሻንን ማስገባት

12. What is the highest level of education you have achieved,

as of today?

የትምህርት ደረጃችንን መምረጥ

13. What is your current marital status?- በአሁን ሰአት ያለን የትዳር

ሁኔታ መምረጥ

14 . Number of Children - የልጅ ብዛት በቁጥር መጻፍ

እያንዳንዱ የተወለዱ ሕጻናት እንዲሁም የማደጎ ልጆች፣ የእንጀራ ልጆች

በእርስዎ ፎርም ውስጥ እያንዳንዱ ያላገቡ ህጻናት, ምንም እንኳን ልጅዎ

ከእርስዎ ጋር አብረው ባይኖሩም መሞላት አለባቸዉ።

»በመጨረሻም continue በማለት Confirmation Number ያለበትን

ወረቀት ፕሪንት በማድረግ ማስቀመጥ እና በ Confirmation Number ን

DV-2023 ሲወጣ ማየት እንችላለን።

DV-2023 Submission Confirmation : Entry success

በዚ መሰረት ፎርሙን በመሙላት እድላችሁን መሞከር ትችላላችሁ ፔጃችንም

መልካም እድል ይመኝላቹሀል

ይሄን መረጃ ለወዳጆ ሼር በማድረግ ማስተላለፍ ትችላላችሁ

Congratulation

 ክቡር አቶ ደምስ ገብሬ የጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ ሆነው  በመሰየሞ የደቡብ ሶዶ ወረዳ የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት ማኔጅመንት አካላትና ባለሙያዎች  የተሰማቸውን ደስታ እየገለፁ መልካም የሥራ ዘመን እንዲሆንልዎ ከልብ እንመኛለን!!!



የደቡብ ሶዶ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት

  መግቢያ የወረዳው ሳይንስናኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ / ቤት የተቋቋመበት ዋናው ምክንያት በወረዳው የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በማልማትና በሁሉም ስፍራ በስፋት በመጠቀም የህብረተሰቡን ኑ...