✳️ Facebook ላይ ማወቅ ያሉብን ጠቃሚ ነገሮች።💡


 🌀1 Facebook በ Data ስትጠቀሙ ብዙ ብር  እንዳይበላባቹ ለማድረግ።


💠 በመጀመሪያም ሶስት ሰረዟን በመንካት ወደታች ወረድ ትላላችሁ ከዛ Data saver የሚል አለ እሱን ስትነኩት Data saver mode የሚል አለ እሱን On በማድረግ ብር እንዳይበላባቹ ማድረግ ትችላላችሁ።


🌀2 Face book ላይ Game መጫወት ለምትፈልጉ ደሞ።


💠 አሁንም ቀላል ነዉ ስቴፑ ሶስት ሰረዟን ትነኩ እና ወረድ ስትሉ Game የሚል አለ እሱን ስትነኩት ሶስት አይነት አማራጭ ይመጣላችኋል ከዛ ሁለተኛ ላይ ያለዉን Play የሚለዉን ንኩት ከዛ እሱን ስትነኩት  የተለያየ ጌሞችን ያመጣላችኋል ከዛ መርጣችሁ መጫወት ነዉ። 


🌀3 Face book ፕሮፋይላችሁን አቆላለፍ ።


💠 በ መጀመሪያም ወደ Setting ትገባላችሁ ከዛ ወረድ ስትሉ Audience and Visibility የሚለዉ ስር Profile Locking የሚል አለ እሱን ስትነኩት ከታች ጋር Lock your profile የሚል ይመጣላችኋል እሱን በመንካት መቆለፍ ትችላላችሁ።


🌀4 Online ሆናችሁ ግን ሌላ ሰዉ Online መሆናችሁን እንዳያዉቁ ለማድረግ።


💠 ወደ Setting ትገቡና Audience and Visibility የሚለዉ ስር Active status የሚል አለ እሱን ስትነኩት Show when you're active የሚል ይመጣላችኋል እሱን off አድርጉት ከዛ ማንም ሰዉ Online መሆናችሁን አያዉቅም


🌀5 የ Social media አካዉንቶቻችንን ፕሮፋይላችን ላይ እንዴት ማስቀመጥ እንችላለን ?


💠 በመጀመሪያም ወደ ምንጠቀምበት Browser በመግባት www.Facebook.com በማለት Login አድርገን ወደ አካዉንታን እንገባለን ከዛ ወደ ፕሮፋይላችን እንገባለን ከዛ Edit public Details የሚለዉን እንነካለን ከዛ Links የሚል አዲስ Option ይመጣልናል እሱን ስንነካዉ ሌላ አማራጭ ሶስተኛ ቦታ ላይ ያመጣልናል Social links የሚል ያመጣልናል እሱን ስንነካዉ የተለያየ የ Social media ዝርዝር ያመጣልናል ከዛ የምንፈልገዉን መርጠን ከ ጎኑ የዛን አካዉንት ስም ሊሆን ይችላል Username በማስገባት መጠቀም እንችላለን ከዛ ከታች ጋር Save የምትለዋን መንካት እንዳይረሳ 

 Nb: ይሄን ሁሉ የምናደርገዉ በምንጠቀምበት Browser ነዉ።


🌀6 ወደፈለግነዉ ቋንቋ ለመቀየር 


💠 ወደ Setting እንገባለን ከዛ Preference የሚለዉ ስር Language የሚል አለ እሱ ስር ገብተን ወደ ፈለግነዉ ቋንቋ መቀየር እንችላለን ( አማርኛ , ኦሮምኛ ) ከምናቃቸዉ ዉስጥ የመሳሰሉትን ማግኘት እንችላለን ።


🌀7 እንዴት ማንም ሰዉ Tag እንዳያደርገን ማድረግ እንችላለን።


💠 ወደ Setting ከዛ Profile and tagging የሚለዉን እንነካለን ከዛ መጀመሪያ ላይ ያለዉን Who can post on your profile ? የሚለዉን እንነካለን ከዛ Friends ላይ ከነበረ Only me የሚለዉ ላይ በማድረግ ማንም ሰዉ Tag እንዳያደርገን ማድረግ እንችላለን ።

@SSWSIT

✳️ ሌላ ሰው የፌስቡክ አካውንታችሁን ሲጠቀም እንዴት ፌስቡክ በሞባይል ስልካችሁ ሚሴጅ (SMS) እንዲልክልን ማድረግ እንደምትችሉ እንይ:-

💠 ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መንገዶች ተጠቅማቹ ደህንነታቹን መጠበቅ ትችላላቹ:-


1. ውደ ፌስቡክ አካውንቶ ይግቡ...


2. የ ፌስቡክ “Settings”⚙️ ዉሰጥ ይግቡ....


3. ከዛም “Settings” ውሰጥ በ ግራ በኩል ከሚመጡት ምርጫዎች “Security & Login” የሚለውን ይምረጡ...


4. ቀጥሎ ከሚመጡት ምርጫዎች “Get Alerts About Unrecognize logins”🔔 የሚለውን ውስጥ እንገባለን...


5. “Text messages” ከሚለው ስር

“Edit" የሚለውን ክሊክ እናረጋለን...


6. በመቀጠል “Get Text Message Alerts At” የሚለው ጋር እንነካለን በመቀጠል ከታች Save ብለን እንወጣለን ማለት ነው።


💠 ቀደም ብለው ለ ፌስቡክ የሞባይል ቁጥሮን ያልሰጡ ከሆነ ግን “Connect Your Phone Number” የሚለውን ላይ በመግባት የሞባይል ቁጥሮን ያስገቡ ከዛም በሞባይሎ የሚላከውን ቁጥር በሚመጣው ሳጥን ውስጥ ያስገቡ (Verify) ያድርጉ ከዛም “Save Changes” የሚለውን ክሊክ ያድርጉና ይውጡ አለቀ፡፡

 ከአሁን በኋላ አካውንቶ በአዲስ "Browser" በተከፈተ ቁጥር ሚሴጅ ይላክሎታል።

@SSWSIT

የደቡብ ሶዶ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት

  መግቢያ የወረዳው ሳይንስናኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ / ቤት የተቋቋመበት ዋናው ምክንያት በወረዳው የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በማልማትና በሁሉም ስፍራ በስፋት በመጠቀም የህብረተሰቡን ኑ...