በቀን 23/07/2014 ዓ.ም ማለትም በዕለተ አርብ በሁለት የት/ት ክላስተሮች የሳይንስና ፈጠራ ሥራዎች ኤግዚቢሽን ተከበረ፤ የአንደኛው ክላስተር ስም፦ ጎጌቲ ክላስተር የሚባል ሲሆን በዚህም ክላስተር አምስት ት/ቤቶችን አቅፎ የሚይዝ ክላስተር እንደሆነና በዛሬው ዕለት ከዚህ ክላስተር ኤግዚቢሽኑን ለመሳተፍ የመጡ ተማሪዎች የመክፈቻ ንግግር የክላስተሩ ሱፐርቫይዘር የሆኑት መ/ር ደበበ ታደሰ በማድረግ በዚህ ክላስተር ት/ቤቶች የጋራ የሆነ ልምድ የሚያገኙበትና ችግር ፈቺ የሆነ ፈጠራ ጎልቶ የሚታይበት እንደሆነ በማውሳት አክለውም በዚህ ኤግዚቢሽን ተማሪዎች ከተለያየ ት/ቤት በመጡ ተማሪዎች የሚያገኟቸው እውቀት፣ ክህሎት እንዲሁም ልምድ ቀላል እንዳይደለ በመግለፅ ይህን ዕድል በዋዛ መመልከት እንደሌለባቸው በማሳሰብ የኤግዝቢሽኑ መጀመር ይፋ በማድረግ የፈጠራ ሥራዎች እንዲጎበኙ እና ተማሪዎች በሰሯቸው የፈጠራ ሥራዎች ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡ ተደርጓል። በተጨማሪም በዚህ ክላስተር እስከ 40 የሚሆኑ የፈጠራ ሥራዎች የታዩበትና ዕለቱም በጥያቄና መልስ ውድድር እንዲሁም በውይይት ተከብሮ ውሏል።
በፕሮግራሙ ማጠቃለያ ላይ የደቡብ ሶዶ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት በሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ሥራዎች ባለሙያ ተወክለው የተገኙት የፅ/ቤቱ ባለሙያ የሆኑት አቶ ናትናኤል ይልማሽዋ በቀረቡት የፈጠራ ሥራዎች ላይ በልጆቹ አቅምና ደረጃ አንፃር አድናቆታቸውን በመቸር ከዚህም በላይ መስራትና ማደግ እንደሚቻል የገለፁ ሲሆን በተሳታፊዎች ለቀረበላቸው አስተያየቶች ተገቢውን ምላሽና ተሞክሮ በመስጠት ንግግራቸውን ቋጭተዋል። በጎጌቲ ክላስተር የኤግዚቢሽኑ የመጨረሻ መርሐ ግብር የነበረው በፈጠራ ሥራዎች ለተሳተፉ ተማሪዎችና ለየት/ቤቱ የፈጠራ ሥራ ክበባት የምስክር ወረቀት በመስጠት ፕሮግራሙ ተጠናቋል።
በሁለተኛው ክላስተር ደግሞ፦ ጎሴ ሳለን ክላስተር የሚባል ሲሆን በዚህም ክላስተር አራት ት/ቤቶችን አቅፎ የሚይዝ ክላስተር እንደሆነና በዛሬው ዕለት ከዚህ ክላስተር ኤግዚቢሽኑን ለመሳተፍ የመጡ ተማሪዎች የመክፈቻ ንግግር ከወረዳው የት/ቤቶች ፅ/ቤት ተወክለው የተገኙት አቶ አውግቾ ከበደ በማድረግ በዚህ ክላስተር ት/ቤቶች የጋራ የሆነ ልምድ የሚያገኙበትና ችግር ፈቺ የሆነ ፈጠራ የሚንፀባረቅበት እንደሆነ በማውሳት በተጨማሪም በዚህ ኤግዚቢሽን ተማሪዎች ከተለያየ ት/ቤት በመጡ ተማሪዎች የሚያገኟቸው እውቀት፣ ክህሎት እንዲሁም ልምድ እንደሚጠቅማቸው በመግለፅ የኤግዝቢሽኑ መጀመር ይፋ በማድረግ የፈጠራ ሥራዎች እንዲጎበኙ እና ተማሪዎች በሰሯቸው የፈጠራ ሥራዎች ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡ ተደርጓል። በተጨማሪም በዚህ ክላስተር እስከ 33 የሚሆኑ የፈጠራ ሥራዎች የታዩበትና ዕለቱም በጥያቄና መልስ ውድድር እንዲሁም በውይይት ተከብሮ ውሏል። በፕሮግራሙ ማጠቃለያ ላይ የደቡብ ሶዶ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት በሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ሥራዎች ባለሙያ የሆኑት አቶ ሀብታሙ ባልቻ በቀረቡት የፈጠራ ሥራዎች ላይ ከዚህም በላይ መስራትና ማደግ እንደሚቻል የገለፁ ሲሆን በተሳታፊዎች ለቀረበላቸው አስተያየቶች ተገቢውን ምላሽና ተሞክሮ በመስጠት ንግግራቸውን ቋጭተዋል። በጎሴ ሳለን ክላስተር የኤግዚቢሽኑ የመጨረሻ መርሐ ግብር የነበረው በፈጠራ ሥራዎች ለተሳተፉ ተማሪዎችና ለየት/ቤቱ የፈጠራ ሥራ ክበባት የምስክር ወረቀት በመስጠት ፕሮግራሙ ተጠናቋል። በፅ/ቤቱ ባለሙያዎች በቀረበላቸው ሪፖርት መሠረት የደቡብ ሶዶ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ደመላሽ ውዴ ይሄ ጅምር እንደሆነና በቀጣይ ከት/ቤቶች ፅ/ቤት ጋር በመተባበር በወረዳ ደረጃ እንደሚከበር በማውሳት በተጨማሪም የፈጠራ ሥራዎቹ በቴክኖሎጂ የታገዙ እንዲሆኑና ከዛም ልቆ የማኅበረሰቡ ችግር እንዲፈታ ፅ/ቤታቸው የቴክኒካል ድጋፍ እንደሚያደርግ አሳስበው ኤግዚቢሽኑን ያከበሩ ት/ቤቶች በማመስገን ሀሳባቸውን አጠናቀዋል።


