✴️ ለመጀመርያ ጊዜ ኢንተርኔት አግኝተህ "Google" ላይ "Search" ያደረከው ነገር ምንድነው❓

  📍የአሜሪካዋ የቴክኖሎጂ መናገሻ በምትባለው "San Francisco" "Silicon Valley" ውስጥ የሚገኘው "Google" ኩባንያን ለየት የሚያደርገው የቢሮው ሁኔታ እና የሰራተኞቹ የአሰራር መንገድ ነው። 


📍ተቀጣሪዎች "....በዚህ ሰዓት ውጣ፣ በዚህ ሰዓት ግባ ፣ ከዚህ እስከ እዚህ ሰዓት ስራ፣ ፊርማ ፈርም፣ እዚህ ተቀመጥ ፣ ይሄንን አትጠይቅ፣ ይሄንን አትንካ፣ ይሄንን ብቻ ስራ!...." ምናምን መባል የለባቸውም! እንደዚህ አይነት ኃላ ቀር አሰራሮች ለብዙ አመታት ውጤት አላመጡም!፣ ፈጠራን አላበረታቱም!፣ ሰራተኛውንም አሰሪውንም አልጠቀሙም!" ብሎ የሚያምነው የ "Google" ኩባንያ የራሴ አሰራር፣ የራሴ የስራ ፍልስፍና አለኝ ይላል! በዚህም ፍልስፍና እጅግ ውጤታማ ሆኗል!


📍የመጀመርያው ድርጅቱን ከስራ ቦታ ይልቅ ሁሉም ነገር የተሟላለት መኖርያ ቤት የሚመስልበትን መንገድ ፈጠሩ። የተለመደውን የቢሮ ቅርፅ አስወገዱ! ድርጅቱ ውስጥ የአለቃ እና የሰራተኛ ወንበር የሚባል ነገር የለም። ሁሉም ቢሮ ክፍት ነው። ሁሉም የፈለገበት ቦታ ላይ ተቀምጦ መስራት ይችላል! የግል ንብረት፣ የግል ኮምፒውተር፣ የግል ወንበር ምናምን የለም! ማንም የምንም ነገር ባለቤት አይደለም! ሁሉም ነገር የሁሉም ንብረት ነው። 


📍የሰራተኞቹን የፈጠራ ብቃት ለመጨመር እና አዕምሯቸው የተፍታታ እንዲሆን በማሰብ የሚዝናኑባቸው እንደ ፑል፣ ቴኒስ፣ ጆተኒ፣ ጎልፍ፣ ዲጅታል ጌም መጫወቻዎች፣ መዋኛ ገንዳዎች እና የሙዚቃ መሳርያዎች በየቦታው አሉ። አንድ ሰራተኛ በፈለገበት ሰዓት መጫወት እና መዝናናት ይችላል። 


📍ስራህን ስትሰራ የተሻለ ስሜት እንዲሰማህ ውሻህ ወይም ድመትህን ጭምር ይዘህ መሄድ ትችላለህ። ድርጅቱ ገደብ (Limitation) የሰዎችን የመፍጠር "tendency" ይቀንሳል! ብሎ ያምናል። 


📍ውስጡ ከ 25 በላይ ትልልቅ ካፍቴርያዎች እና ሬስቶራንቶች ያሉት "Google" ሰራተኞቹ በፈለጉት አጋጣሚ ያሻቸው ምግብ እንዲቀርብላቸው ያደርጋል። አንድ ሰራተኛ ከ 200 ጫማ (60 ሜትር) በላይ ከምግብ መራቅ የለበትም በሚል ፍልስፍናም ድርጅቱ ያምናል! "የራበው አይሰራም! ሁሉም ነገር የቀረበለት ሰራተኛ ደግሞ ትኩረቱን ወደ ስራ እና ስራ ብቻ ማድረግ ይችላል!" በሚል አመለካከት ያምናሉ።


📍ሰራተኞቹ አዓምሯቸው ከተወጣጠረ እራሳቸውን ለማፍታታት በቢሮ ውስጥ ማሳጅ የሚደረጉባቸው ክፍሎች እና የሰለጠኑ እና ፍቃድ ያላቸው የማሳጅ ቴራፒስቶች ዝግጁ ሆነው ይጠብቋቸዋል! 


📍ለአካባቢያዊ አየር ጥበቃ ካላቸው ትኩረት የተነሳ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰራተኞቹ ከስራ ቦታ ወደ ቤት/ከቤት ወደ ስራ ቦታ የሚመላለሱት የልቀቅ መጠናቸው እጅግ በጣም ዝቅተኛ በሆኑ ባሶች ነው። እያንዳንዱ ሰራተኛ የራሱን መኪና እየነዳ ቢመላለስ በአመት ሊለቀቅ የሚችለውን ከ 20 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ ልቀት መቀነስ ተችሏል። ግቢ ውስጥ ሰራተኞች የሚንቀሳቀሱት በሳይክል ነው! ይህም ልቀትን ከመቀነስ አንፃር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል! 


📍በቅጥር ግቢው የሚበቅለውን ሳር/አረም ለማስወገድ "Google" ማሽኖችን" ሳይሆን "ፍየሎችን" ነው የሚጠቀመው! በየግዜው ፍየሎችን እየተከራየ በግቢው ውስጥ የሚበቅለውን ሳር/አረም እንዲግጡለት ያደርጋል! አንድ ሰራተኛ እየሰራ በአጠገቡ ፍየል ሲያልፍ አይደንቀውም!😃 ሰራተኞቹ እንደውም እነዚህን ፍየሎች ማየታችን የፈጠራ አቅማችንን ጨምሮልናል ይላሉ።


📍"Google" ዋናው ኩባንያ አጠገብ ለምትገኘው "Mountain View" ለምትባል አነስተኛ ከተማ ነዋሪዎች በሙሉ በነፃ ዋይ ፋይ እንዲያገኙ እና ኢንተርኔትን ያለምንም ገደብ እንዲጠቀሙ አድርጓል።


📍በድርጅቱ የተቀጠረ ሰራተኛ ህይወቱ ቢያልፍ ሚስት ወይም ባል የሟች 50% ደሞዝን ለ 10 ዓመታት እንዲከፈላት/እንዲከፈለው ይደረጋል። 


📍በአጠቃላይ በድርጅቱ ውስጥ ሰራተኞች ላፕቶፓቸውን ይዘው ሸርተቴ እና ዥዋዥዌ ሲጫወቱ ማየት ብርቅ አይደለም።


📍"Larry page" እና "Sergey Brin" በተባሉ በ "Stanford University" የ "PHD" ተማሪዎች የተመሰረተው "Google" ኩባንያ አሁን ላይ ከ 500 ቢልዮን ዶላር በላይ "worth" የሚያደርግ ሲሆን የዓለማችን "Most Visited website" ነው። የዛሬ 22 ዓመት ሲመሰረት የመጀመርያ ቢሮው የክራይ ጋራዥ ውስጥ ነበር። በወቅቱ በተከራዩት ገራዥ ውስጥ 16 ሰራተኞች ብቻ ነበራቸው! አሁን ላይ በዓለም የተለያዩ 50 ሃገራት 70 ግዙፍ ቢሮዎች እና በ ብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰራተኞች አሉት። 


◽️የመጨረሻ! 


📍"Google" በመጀመርያ ስፔሊንጉ "Googol" የነበረ ሲሆን መስራቾቹ የድርጅቱን "Domain" ለማስመዝገብ ሲሄዱ በተፈጠረ የስፔሊንግ ስህተት ነው "Google" ተብሎ የቀረው። በነገራችን ላይ በአማካይ በቀን "1 ቢልዮን" ነገሮች "Google" ላይ "Search" ይደረጋሉ።

===>

 📍ብዙ ጊዜ ሶፍትዌርኦችን ስንገዛ "crack" የተደረጉ ናቸው። ይሄም የሆነው አንድም  የመግዛት አቅም ስለሌለን ሁለትም online ግብይት በኛ ሀገር ስላልተጀመረ ነው። 

📍 አንድ ሶፍትዌር crack የተደረገ ነው የሚባለው ሶፍትዌሩ በሀከሮች ሀክ ተደርጎ ሶፍትዌሩ አገልግሎቱን በነጻ እንዲሰጥ ማድረግ ሲቻል ነው።  

📍እነዚህን ሶፍትዌሮች ለመጫን ግን ብዙ ጊዜ ስንቸገር እንታያለን። ለዛሬ Crack የተደረጉ ሶፍትዌሮችን ያለ ምንም ችግር የምንጭንበትን መንገድ አሳያቹሀለው። 


🔥 Step1 ፦  በመጀመሪያ ደረጃ ኢንተርኔት ማጥፋታችንን ማረጋገጥ አለብን። ብዙ ጊዜ የሶፍትዌር ካምፓኒዎች originality validate የሚያደርጉት በዚህ ስለሆነ ነው። ቀጥሎ አንቲ ቫይረስ ካለን disable ማድረግ አለብን አለበለዚያ crack የሆነውን የሶፍትዌር ፋይል ከቫይረስ ጋር በመመደብ ከኮምፒውተራችን ሊያጠፋው ወይንም ሊያስወግደው ይችላል።

🔥 Step 2 ፦ ሶፍትዌራችንን run አርገነው ከጫንን በኋላ launch/ መክፈት/ የለብንም። መመሪያው ላይም  tick ✔️ ተደርጎ ከሆነ untick ➖ ማድረግ ይኖርብናል።

🔥Step 3 ፦ በ crack መልክ የመጣ ሶፍትዌር ከሆነ crack ፋይል ውስጥ ያሉትን ፋይሎች copy አድርገን ሶፍትዌራችንን የጫንበትን location ከፍተን paste ማድረግ ከዚያም overwrite ላርገው የሚል ምርጫ ሲመጣልን የስ(yes) የሚለውን ምርጫ መምረጥ። (ብዙውን ጊዜ ሎኬሽኑ የሚገኘው local C /program file 86 ውስጥ ነው ።  አልያም የጫነው ሶፍትዌር icon ላይ right click በማድረግ open location የሚለውን መምረጥ






✴️ ኒውራልሊንክ ኩባንያ ቴክኖሎጂውን በሰው ላይ ለመሞከር እየተዘጋጀ ነው፡፡


📍የቢሊየነሩ ኤለን መስክ ንብረት የሆነው ኒውራልሊንክ ኩባንያ በዝንጀሮ ላይ ሞክሮ ውጤታማነት አስመዝግቧል፡፡ በመሆኑም ቴክኖሎጂውን በሰው ላይ ለመሞከር እየተዘጋጀ መሆኑን አስታውቋል፡፡ 


📍ኒውራልሊንክ በሰው ልጅ አዕምሮ ውስጥ በሚቀበር የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ማይክሮቺፕ አማካኝነት ኮምፒዩተር እና ተያያዥ ማሽኖችን ያለእጅ ንክኪ በአዕምሮ ብቻ የማዘዝ አቅምን ይሰጣል፡፡


📍ቴክኖሎጂው በተለያየ ምክንያት ሙሉ ሰውነታቸውን ማንቀሳቀስ ለማይችሉ ሰዎች ስማርት ስልኮቻቸውን እና ተያያዥ መሣሪያዎችን እንዲጠቀሙ ያስችላል ሲል ዘጋርዲያን ዘግቧል፡፡


📍በአዕምሮ የሚቀመጠውን ማይክሮቺፕ ገመድ አልባ በሆነ ሁኔታ የኃይል ሙሌት (ቻርጅ) ማድረግ የሚቻል እና ምቾት የማይነሳ መሆኑን የኩባንያው መስራች ኤለን መስክ በተደጋጋሚ ሲነገር ይደመጣል፡፡

  

📍ኩባንያው በሰው ላይ ሊያደርግ ላቀደው የመጀመሪያ ሙከራ የሚያስፈልገውን የሰው ኃይል ለማሟላት እንቅስቃሴዎች መጀመሩን ዘገባው አመላክቷል፡፡



✴️ በ አንድ ቀን 40 ሺህ ዛፎችን የሚተክለው ድሮን 🌴

🔥40 ሺህ ዛፎችን የሚተክለው ድሮን ኤር ሲድ የተሰኘው የአውስትራሊያ የባዮቴክ ኩባንያ እነዚህ ራሳቸውን ችለው የሚበሩ ድሮኖች ከአየር ላይ በቀን ከ40,000 በላይ የዘር ፍሬዎችን በመትከል የደን ጭፍጨፋን መቋቋም እንደሚችሉ ተናግሯል።


🔥የኤር ሲድ ቴክኖሎጂስ የደን መጨፍጨፍን ለመዋጋት አዲስ መንገድ ቀይሷል፡ አዳዲስ ዛፎችን ለመትከል ራሱን የቻለ የኢኮ-ድሮን ይዞ ብቅ ብሏል። በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የሚንቀሳቀሱት እና ራሳቸውን ችለው የሚሰሩት ድሮኖች ከሰማይ ላይ ወደ መሬት የሚተኮሱ ልዩ የዘር ፍሬዎች የተጫኑ ናቸው ሲል ዩሮ ኒውስ ዘግቧል።


🔥የኤር ሲድ ቴክኖሎጂ መስራች አንድሪው ዎከር እንደዚህ ሲል ተናግሯል “እያንዳንዱ ሰው አልባ ድሮኖች በቀን ከ40,000 በላይ የዘር ፍሬዎችን መትከል ይችላሉ። ከተለምዷዊ ዘዴዎች ጋር ሲነጻጸር ይህ 25 እጥፍ ፈጣን እና 80% ርካሽ ነው።’’ ድሮኑ የዛፍ ዘሮችን ከሰማይ ላይ ወደ ምድር በመተኮስ እንዲተከል ያደርጋል የተባለ ሲሆን፤ ይህ የድሮን ቴክኖሎጂ በዓመት በሚሊየን የሚቆጠሩ ዛፎችን ለመትከል የሚያስችል ነው ተብሏል።


🔥ድሮኖቹ በየቀኑ የዘር ፍሬ ለመትከል ከመውጣታቸው በፊት ከሚበሩበት አካባቢ ጋር የሚጣጣሙ የዘር ፍሬዎች ይጫናሉ። እንደ እውነቱ ከሆነ፣ እነዚህ እንክብሎች ከቆሻሻ ባዮማስ የተሠሩ በመሆናቸው፣ ወፎች ወይም ነፍሳት ወደ ዘሩ እንዳይደርሱ ስለሚከላከሉ ለሥነ-ምህዳር ተስማሚ ናቸው። ድሮኑን ዲዛይን ያደረገው የአውስትራሊያው ኤርሲድ ኩባንያ፤ ዘር ጣዩ ድሮን በቀን እስከ 40 ሺህ ዛፎችን መትከል የሚችል መሆኑን አስታውቋል።


🔥ድሮኑ ዘሩን ከተለያዩ የዱር አራዊት ዓይነቶች ይጠብቃል፣  ዘሩ ከበቀለ በኋላ ይደግፋል እና ሁሉንም የሚፈልጓቸውን ንጥረ ነገሮች እና ማዕድናት ያቀርባል፤ አንዳንድ ፕሮባዮቲክስ በመስጠት የመጀመሪያ ደረጃ እድገትን ያፋጥናል። በቴክኖሎጂውን በመጠቀምም እስካሁን በአውስትራሊያ፣ በካናዳ እና በደቡብ አፍሪካ ከ50 ሺህ በላይ ዛፎችን መትከል መቻሉንም ኩባያው አስታውቋል።


🔥በከባቢ አየር ውስጥ ያለውን የካርቦን ዳይኦክሳይድ መጠን ለመቀነስ እና የአየር ንብረት ለውጥን ለመቀነስ ይህ የደን መልሶ ማልማት ጥረት “ለሚቀጥለው ትውልድ የተመቻቸ እና ጥሩ አየር ያላት ምድርን ለመፍጠር መደረግ ያለበት ነው በማለት ዎከር ተናግሯል። የኤር ሲድ ቴክኖሎጂዎች በፈረንጆቹ 2024 እስከ 100 ሚሊዮን አዳዲስ ዛፎችን የመትከል አስደናቂ ግቡ ላይ እንደሚደርስ እርግጠኛ ናቸው።

ኤቲኤም በምንጠቀምበት ጊዜ ደህንነታችንን ለመጠበቅ የሚረዱ ወሳኝ ጠቃሚ ምክሮች💳‼️

 ኤቲኤም በምንጠቀምበት ጊዜ ደህንነታችንን ለመጠበቅ የሚረዱ ወሳኝ ጠቃሚ ምክሮች💳‼️


✅ ኤቲኤም ሲጠቀሙ ሊጫኑ የሚችሉ መሳሪያዎችን ይፈትሹ። እነዚህ መሳሪያዎች የካርድ አጭበርባሪዎች ገንዘብ ለማውጣት ሲያስገቡ የካርድዎን መረጃ ለመስረቅ የሚጠቀሙበት ነገር ነው። የካርድ አንባቢው የላላ እንደሆነ ወይም ከባንኩ የንግድ ምልክት የተለየ ቀለም እንደሆነ ለመወሰን ትኩረት ይስጡ. የቁልፍ ሰሌዳ አዝራሮችን፣ ጭረቶችን፣ የተበላሹ ወይም ያልተስተካከሉ ቁርጥራጮችን እንዱሁም ቁጥሮችን ሲጫኑ የመቋቋም ችሎታ ከሌለው እነዚህ ብዙውን ጊዜ እጭበርባሪው ከኤቲኤም ጋር እንደተያያዘ የሚያሳዩ ምልክቶች ናቸው።


✅ አካባቢህን አስተውል በተለይም በምሽት 🌙 ማንኛውም አጠራጣሪ እንቅስቃሴ ካዩ (አንድ ሰው ጥቂት ጫማ ርቆ የሚጠብቅ ወይም በዙሪያው ምንም መብራቶች ከሌሉ) ያንን ማሽን ከመጠቀም ይቆጠቡ እና ሌላ ህዝብ በሚበዛበት አካባቢ ያግኙ።


✅ ፒንዎን በሚያስገቡበት ጊዜ ሰውነቶን የኤቲኤም ኪቦርድ "መከለያ" ይጠቀሙ።


✅ ሁልጊዜ ደረሰኞችዎን ወይም የግብይት መዝገቦችን ይዘው ይሂዱ።


✅drive-up ATM እየተጠቀሙ ከሆነ የተሳፋሪዎች መስኮቶች መዘጋታቸውን እና ሁሉም በሮች መቆለፋቸውን ያረጋግጡ።


✅ ካርዱን 💳 ወደ ኤቲኤም ቦታ ስንቃረብ ዝግጁ ማድረግ።



 ቀን 22/04/2014 ዓ.ም

ኬላ
የደቡብ ሶዶ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት በወረዳው ለሚገኙት ተቋማት (ሴክተሮች) ባለሙያዎች መሠረታዊ የኮምፒዩተር ክህሎት ስልጠና ሰጠ።
የዕለቱን መርሀግብር የደቡብ ሶዶ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ደመላሽ ውዴ ንግግር በማድረግ የጀመሩት ሲሆን ይህ ስልጠና እንደ አዲስ ተቋም ይበል የሚያሰኝ ተግባር ነው፤ ምክንያቱም ልምድ ባላቸው ወረዳዎች ሊሰጥ ያልተቻለውን ይህ መሰረታዊ የኮምፒዩተር ስልጠና በእኛ ወረዳ በአጭር ጊዜ ውስጥ መዘጋጀቱ ተቋሙ ባለሙያውን ብሎም ማኅበረሰቡን ለማገልገል ቆርጦ መነሳቱን ይገልፃል ብለዋል። አክለውም የመንግስት ወጪ የኅብረተሰቡ ወጪ ነውና የወጪ ብክነትን ለመቀነስ ተግባሩ የሚጀምረው እንዲህ ዓይነቱ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ስልጠና በመስጠት ይጀምራል።
ፅ/ቤቱ ከቡኢ ኢንደስትሪያል ኮሌጅ አንድ አሰልጣኝ በመጋበዝ ከፅ/ቤቱ ባለሙያ ጋር በመተባበር ስልጠናው ተሰጥቷል። የፅ/ቤቱ ኃላፊ ለአሰልጣኞቹ ማለትም መ/ር ሀይለሚካኤል እና ለአቶ ናትናኤል ይልማሽዋ እንዲሁም ለነበራቸው የመማር ፍቅር ጉጉት ላሳዩት ለሰልጣኞቹ ምስጋናቸውን ችረዋል።
ሰልጣኞቹ ምንም እንኳን በሙያው መስመር ብንሆንም የረሳንውን እንድናስታውስ ረድቶናል፤ በተጨማሪም አዳዲስ የቴክኖሎጂ ሀሳቦችን እንድናገኝ ጠቅሞናል ሲሎ ሀሳባቸውን በድስታ የገለፁት ሰልጣኞቹ ይህ ስልጠና ቀጣይነት ይኑረው በማለት አስተያየታቸውን ገልፀዋል።
በመጨረሻም የፅ/ቤቱ ኃላፊ ስልጠናው ላይ የነበራቸው ቆይታ እንዴት እንደነበረ በመጠየቅ የወሰዱትን ስልጠና በተቋማቸው እንዲሁም በተሰማሩበት ቦታ በመተግበር ኅብረተሰቡን እንዲያገለግሉ አደራቸውን ለሰልጣኞቹ በመግለፅና ከዚህ በበለጠ ተጠናክሮ ስልጠናው እንደሚቀጥል በመግለፅ የዕለቱን መርሀግብር እንደተቋጨ ገልፀዋል።
ዘገባው የደቡብ ሶዶ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት ነው።





የደቡብ ሶዶ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት

  መግቢያ የወረዳው ሳይንስናኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ / ቤት የተቋቋመበት ዋናው ምክንያት በወረዳው የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በማልማትና በሁሉም ስፍራ በስፋት በመጠቀም የህብረተሰቡን ኑ...