የደቡብ ሶዶ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት

 መግቢያ

የወረዳው ሳይንስናኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ /ቤት የተቋቋመበት ዋናው ምክንያት በወረዳው የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በማልማትና በሁሉም ስፍራ በስፋት በመጠቀም የህብረተሰቡን ኑሮ ማሻሻልና ቴክኖሎጂ ለወረዳው እድገት የሚሰጠውን ድጋፍ ማሳደግ ነው፡፡

እንዲሁም ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍን በማሳደግና በፖለቲካዊ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ያለውን አስተዋጽኦ በማጎልበት በወረዳችን የፈጣን ልማትና እድገት ተጠቃሚ እንዲሆን ለማድረግ ነው፡፡

በመሆኑም ወረዳው እስከ ቀበሌ ባሉ መንግስታዊ ተቋማት ውስጥ የሚሰጠው አገልግሎት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈና የተደራጀ እንዲሆንና አገልግሎት አሰጣጡ ዘመናዊ ቀልጣፋና ውጤታማ በማድረግ መልካም አስተዳደርን ማስፈንና የሃብት ብክነትን መቀነስ ነው፡፡

በተጨማሪም በህብረተሰቡ ውስጥ ዘመናዊ የመረጃ ቴክኖሎጂን በመዘርጋትና በማስፋፋት ህብረተሰባችን የግብርና የገበያ፤የጤና፤የትምህርት እና የንግድ መረጃዎችን በአቅራቢያው እንዲያገኝ በማድረግ በገጠርና በከተማው ህብረተሰብ መካከል ያለውን የዘመናዊ መረጃ ቴክኖሎጂ ክፍተት ማጥበብ ነው፡፡

በተጓዳኝም ፈጣን እድገት ለማረጋገጥ የግሉ ዘርፍ ቴክኖሎጂውን ለማስፋፋት የሚጫወተውን ሚና ግምት ውስጥ በማስገባት የሚጎለብትበትንና የሚስፋፋበትን መንገድ ማጠናከር አንዱ ዓላማው ነው፡፡

የጽ/ቤቱ ራዕይ፣ተልዕኮ፣ዓላማዎችና ዕሴቶች

F ተልዕኮ

*      በወረዳው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ጉልህ አስተዋፅኦ የሚያደርጉ የሳይንስና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ስራዎችን ለህብረተሰቡ በአግባቡ በማልማት፣በመተግበርና በማስፋት ወረዳዊ ብሎም አገራዊ የተወዳዳሪነት አቅምና በቴክኖሎጂ የዳበረ የአሰራር ስርዓት መፍጠር ነዉ፡፡

ራዕይ

*      2030 በወረዳው ውጤታማ የሆኑ የሳይንስና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂዎችን በመፍጥነት የመማር፣የማልማት፤የመፍጠራ፣ስራ የማላመድ በቴክኖሎጂ  የመጠቀም አቅም ተገንብቶ ማየት   

F  እሴቶች

À      በጎህሊናና ቅንልቦና፣

À      የስራ ፍቅርና ትጋት፣

À      ያልተገደበ አስተሳሰብና ምናባዊጉዞ፣

À      ለለውጥ በጋራ መስራት፤

À      ውጤታችንም ሆነ ውድቀታችን የጋራችን ነው፤

À      ችግር ፈቺነት፤

À      የማይረካ የመማር ጥማት፤

À      ለትውልድ የሚተላለፍ መሠረት፣

À      ቀልጣፋና ውጤታማ አሰራርናቀጣይነት ያለው መሻሻል፣

ሁሉንም የፅ/ቤታችን የሶሻል ሚዲያዎቻችን ይህንን ሊንክ በመጫን ያገኟቸዋል፦

 https://solo.to/sswsit

የደቡብ ሶዶ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት

  መግቢያ የወረዳው ሳይንስናኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ / ቤት የተቋቋመበት ዋናው ምክንያት በወረዳው የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በማልማትና በሁሉም ስፍራ በስፋት በመጠቀም የህብረተሰቡን ኑ...