☞በአለማችን ይኖራሉ ብለው የማይገምቷቸው አስገራሚ ድረ ገፆች




✔️✔️✔️✔️✔️✔️✔️✔️✔️✔️✔️


☞ በአሁኑ ወቅት መጠኑ ይለያይ እንጂ አንዳንዶቻችን በየቀኑ የኢንተርኔት መረቦችን መቃኘታችን የተለመደ ተግባር ሆኗል።


የምንቃኛቸው ድረ ገፆችም ብዙ ጊዜ የምናውቃቸውን አልያም በጣም ታዋቂዎቹን ነው።


አንዳንድ ጊዜም በፌስቡክ አማካኝነት ያገኘናቸው መረጃዎች አዳዲስ ድረ ገፆችን ያስተዋውቁናል።


እነዚህን አዳዲስ ድረ ገፆችም ጠቃሚ ሆነው ስናገኛቸው ለሌላ ጊዜ እንድንጠቀማቸው ቡክማርክ አድረገን እናስቀምጣቸዋለን።


ከዚህ በታች የተዘረዘሩት 9 ድረ ገፆች ግን ምናልባትም አይተናቸው የማናውቃቸው እና የተለየ አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው ይላል ቴክወርም የተሰኘው የቴክኖሎጂ ድረ ገፅ ዘገባ።


1. 10Minutemail.com


ይህ ድረ ገፅ ለ10 ደቂቃ የሚቆይ የኢሜል አድራሻ ለመክፈት ያስችላል።


ድረ ገፁ የተላላክናቸውን መልዕክቶች እና የኢሜል አድራሻውን ከ10 ደቂቃዎች በኋላ ሙሉ በሙሉ ያጠፋዋል።


10Minutemail.com እንደከፈትነው ምንም ምዝገባ ሳያስፈልገን ራሱ የኢሜል አድራሻ ይሰጠናል።

👇👇👇👇

በተጨማሪም Tempmail ለዚህ ይጠቅመናል አጠራጣሪ ድረገጾች ስንከፍት ኢሜል ሲጠይቁን በዚህ መጠቀም እንችላለን


2. የሀሰት ስም እና አድራሻ ፈጣሪ - Fake Name Generator


በጣም አይነአፋር የሆኑ፣ የግል ጉዳያቸው የሚያስጨንቃቸው እና ትክክለኛ ስማቸውን ይፋ ማድረግ የማይፈልጉ ሰዎች በዚህ ድረ ገፅ አማካኝነት የሀሰት ስም እና ዝርዝር መረጃዎችን መፍጠር ይችላሉ።


Fakenamegenerator.com  


3. አንዳንድ ድረ ገፆች የማይከፍቱት እንዳልከፍታቸው ስለታገድኩ ነው ወይስ ስለማይሰሩ? - Down for Everyone or Just Me


አንዳንድ ጊዜ ኮምፒውተርዎ የተወሰኑ ድረ ገፆችን አልከፍት ሊልዎት ይችላል። እናም በዚህ ድረ ገፅ አማካኝነት እውን ይህ ድረ ገፅ አልከፍት ያለዎት ስለማይሰራ ነው አልያስ ሆን ተብሎ እንዳይከፍቱት ስለተደረገ ነው የሚለውን ማረጋገጥ ይችላሉ።


Downforeveryoneorjustme.com 


4. የቀናት ልዩነትን ለማስላት - Date and Time 


በዚህ ድረ ገፅ ደግሞ በቀናት እና አመታት መካከል ያሉ ልዩነቶችን ለማስላት ይጠቅማል።


ለአብነትም እድሜያችን በቀናት ለማስላት የተወለድንበትን ቀን፣ ወር እና አመት እና የእለቱን ቀን ወር እና አመት በማስገባት በምድር ላይ ለስንት ቀናት ቆይታ እንዳደረግን ማስላት እንችላለን።


የምናሰላው ቀን በአላትን እና ቅዳሜ እና እሁድን አካቶ አልያም ሳያካትት ስንት እንደሆነም ማወቅ ያስችላል።


timeanddate.com 


5. የድረ ገፆችን የፊት ገፅ ምስል ለማስቀረት - Web Capture


የተለያዩ ድረ ገፆችን የፊት ገፅታ ምስል ለማስቀረት እና ወደ JPG/JPEG፣ PNG አልያም PDF ፎርማት ለመቀየር ይህን ድረ ገፅ ይጠቀሙ። 


webcapture.net/  


6. ጎግልን ያለምንም የሀገር ገደብ ለመጠቀም - Google NCR


የጎግል ድረ ገፅን (google.com) ስንከፍት ጎግል ወደየሀገራችን ዶሜን ያስገባናል። ለምሳሌ ጎግልን በኢትዮጵያ ስንከፍት google.com.et ወደሚለው ያሸጋግረናል። ይህም የሚሆነው ጎግል እንደየሀገራቱ የሚከለክለው እና የሚፈቅደው ስላለው ነው።


እናም ጎግልን ያለምንም የሀገራት ገደብ ለመክፈት google.com/ncr ብለን መፈለግ በቂ ነው።


7. የተላኩልን ፋይሎች በቫይረስ የተጠቁ መሆን አለመሆናቸውን ለማረጋገጥ -የተላከልን Virustotal


ከጓደኞቻችን አልያም ከማናውቀው ግለሰብ የሚያጠራጥር ፋይል ከተላከልን እና ከኢንተርነየት በቀጥታ ካወረድነው በዚህ ድረ ገፅ አማካኝነት  ፋይል ቫይረስ መያዙን እና አለመያዙን ማወቅ እንችላለን።


ቪሩስቶታል ነፃ የኢንተርኔት የቫይረስ መመርመሪያ (ስካነር) ነው።


8. በአለማችን እየተከናወኑ ያሉ ወቅታዊ የመረጃ ዘረፋዎችን የሚያሳይ ካርታ - IPviking


በአለም ዙሪያ እየተከናወኑ ያሉ የመረጃ ምንተፋዎች፣ የአይፒ አድራሻዎች፣ የመረጃ ዘራፊዎቹን አድራሻ እና የመሳሰሉ መረጃዎችን http://map.norsecorp.com/#/ በተባለው ድረ ገፅ ላይ መመልከት ይቻላል።


9. Hackertyper


ይህን ድረ ገፅ ከፍተን የተለያዩ ፊደላትን እና ቁጥሮችን ስንጫን መረጃ ዘራፊዎች የሚጠቀሙበትን አይነት ገፅ ይከፍትልናል።


በዚህም ጓደኞቻችን እና ወዳጆቻችን የተለያዩ ድርጅቶችን መረጃዎችን እየሰረቅን ለማስመሰልና ለመሸወድ እንችላለን።


http://hackertyper.net/


10. Password Generator 


ጠንካራ  እና በቀላሉ ብሬክ የማይደረግ የይለፍ ቃል ለፌስቡክ ለኢሜል ለሌሎች ፓስወርድ ለሚጠይቁ በሙሉ ጠንካራ የይለፍ ቃል (ፓስወርድ)  ለመመስረት

 📲 ስልክዎ እንደተጠለፈ የሚያሳዩ ሰባት ምልክቶች

 ▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃


1. የስልክዎ ፍጥነት ከቀነሰ


ተንቀሳቃሽ ስልክዎ ከሌላው ጊዜ በተለየ ትዕዛዞችን ለማከናወን ረዘም ያለ ጊዜ የሚፈጅ ከሆነ፤ ባዕድ ሶፍትዌሮች (ማልዌር) እያስቸገሩት ነው ማለት ነው።


እነዚህ ማልዌር የተባሉት ቫይረሶች ዋነኛ ሥራቸው የስልክዎን አጠቃላይ እንቅስቃሴ ማዘግየት ሊሆን ስለሚችል፤ በአፋጣኝ ማስወገድ ተገቢ ነው።


2. ስልክዎ በጣም የሚግል ከሆነ


ስልክዎት ከተለመደው ከፍ ባለ ሁኔታ የሚግል ከሆነ፤ ችግር አለ ማለት ነው። በፍጥነት እርምጃ ይውሰዱ አልያም ባለሙያ ያማክሩ።


3. የስልክዎ የባትሪ ኃይል ቶሎ የሚያልቅ ከሆነ


ስልክዎ ከፍተኛ ሙቀት አለው ማለት ደግሞ የባትሪው ኃይል ቶሎ ቶሎ ያልቃል ማለት ነው።


ምናልባት ስልክዎ አዳዲስ መተግበሪያዎችንና ሶፍትዌሮችን ለማደስ በሚሞክርበት ወቅት የባትሪውን ኃይል ሊጨርስ ይችላል። ነገር ግን ምክንያቱ ይህ ካልሆነ ስልክዎ ተጠልፎ ሊሆን እንደሚችል ማሰብ አለብዎ።


4. ወደ ማያውቁት ሰው መልዕክት ከተላከ ወይም ከማያውቁት ሰው መልዕክት ከደረስዎ


ብዙ ጊዜ እርስዎ የማያውቋቸው መልእክቶች የሚላኩት በዋትሳፕና በመሳሰሉ መተግበሪያዎች በኩል ሲሆን፤ የሚላከው ደግሞ ወደ ጓደኛዎት አልያም ወደ የማያውቁት ሰው ሊሆን ይችላል።


ወደ እርስዎ የሚላኩ መልዕክቶች ደግሞ ብዙ ጊዜ ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ የሚሉ ማሳሰቢያዎች ይበዟቸዋል።


5. ከበይነ መረብ የሚመጡ ድንገተኛ መልዕክቶች


ስልክዎን በመጠቀም በይነ መረብን (ኢንትርኔት) በሚያስሱበት ወቅት ወደ ሌላ ድረ-ገጽ የሚያሸጋግሩ መልዕክቶች በተደጋጋሚ የሚመጡ ከሆነ የስልክዎ መጠለፍ ነገር እውን ሊሆን ይችላል።


መልዕክቱን ሲጫኑ በአንድ ጊዜ ወደ ሁለትና ሦስት የድህ-ረገጾች አድራሻዎች የሚመራዎ ከሆነ በፍጥነት ይውጡ።


6. አጠራጣሪ መተግበሪያዎችና ገንዘብ ነክ ጥያቄዎች


አንዳንድ ጊዜ እርስዎ ያልገዙት ወይም ከበይነ መረብ ያላወረዱት መተግበሪያ ስልክዎት ላይ ሊመለከቱ ይችላሉ። ምናልባትም የሞባይል ዳታ እና የጽሁፍ መልዕክት ላይ የዋጋ ጭማሪም ሊያስተውሉ ይችላሉ።


የክሬዲት ካርድና የሞባይል ገንዘብ ማንቀሳቀሻ መንገዶችን የሚጠቀሙ ከሆነ ይህ ሁኔታ ለጠላፊዎች ምቹ አጋጣሚ ሊፈጥርላቸው ይችላልና ይጠንቀቁ።


ስለዚህ የይለፍ ቃሎችንና የግል መረጃዎችን ስልክዎት ላይ ባያስቀምጡ ይመረጣል፤ አልያም በጠላፊዎች እንዳይገኝ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል።


7. ያልተለመዱ ድምጾች


የድምጽ ጥሪ በሚያደርጉበት ወቅት ያልተለመዱና ከዚህ በፊት ያልነበሩ ድምጾች የሚሰማዎት ከሆን ምናልባት ስልክዎ የጠላፊዎች ሰላባ ሆኖ ሊሆን ይችላል። ይባስ ብሎም የስልክ ጥሪዎችዎ እየተቀዱም ሊሆን ይችላል።


🏷 መፍትሄዎች

   ━━━━━━

▫️የስልክ ማጽጃዎችን ከታማኝ ምንጭ ማግኘት


▫️እርስዎ የማያውቋቸውን መተግበሪያዎች ከስልክዎ ማጥፋት


▫️ብዙ ሰው የሚጠቀማቸው ነጻ የኢንተርኔት አገልግሎቶችን አለመጠቀም


▫️ስልክዎን በቀላሉ ሊታወቅ በማይችል የይለፍ ቃል መዝጋት


▫️ከማይታወቁ ምንጮች መተግበሪያዎችን አለመጫን


▫️ስልክዎና በስልክዎ ላይ ያሉ መተግበሪያዎችን ቶሎ ቶሎ ማሳደስ (update) 


▫️ስልክ ክፍያዎንና የዳታ አጠቃቀምዎን ይቆጣጠሩ

የደቡብ ሶዶ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት

  መግቢያ የወረዳው ሳይንስናኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ / ቤት የተቋቋመበት ዋናው ምክንያት በወረዳው የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በማልማትና በሁሉም ስፍራ በስፋት በመጠቀም የህብረተሰቡን ኑ...