በመላው ዓለም ዋትስአፕ የማህበራዊ ትስስር መተግበሪያ አገልግሎቱ ተቋረጠ **************************

የዋትስአፕ የመልእክት መላላኪያ መተግበሪያ በኢትዮጵያ እና በመላው ዓለም ባልታወቀ ምክንያት ለተጠቃሚዎች መቋረጡ ተነግሯል።

ዋትስ አፕ መተግበሪያ የሜታ ኩባንያ ንብረት ሲሆን በዓለም ደረጃ ከዛሬ ረፋድ ጀምሮ አገልግሎት መስጠት ማቋረጡን ድርጅቱ አስታውቋል።

በኢትዮጵያም ይህ መተግበሪያ አገልግሎት መስጠት ያቆመ ሲሆን በርካታ የመተግበሪያው ተጠቃሚዎች አገልግሎቱ መቋረጡን በሌሎች የማህበራዊ ትስስር ገጾቻቸው ላይ በመግለጽ ላይ ናቸው።

ኢትዮ ቴሌኮም በበኩሉ፣ የዋትስአፕ አገልገሎት የተቋረጠው በመተግበሪያው አቅራቢ በኩል በገጠመው ችግር መሆኑን ገልጾ፣ በኢትዮ ቴሌኮም በኩል ምንም ዓይነት የኔትወርክ አገልግሎት ዕክል እንዳልተፈጠረ አስታውቋል።

ይሁንና የሜታ ኩባንያ ሆነ ዋትስ አፕ በዛሬው ዕለት ስለተፈጠረው የአገልግሎት መቋረጥ እስካሁን ያሉት ነገር የለም።

ዋትስአፕ በዓለም ዙሪያ ወደ ሁለት ቢሊዮን የሚጠጉ ተጠቃሚዎች እንዳሉት ቢቢሲ ዘግቧል።                                                                              https://t.me/SSWSIT



2022 ምርጥ የካሜራ ጥራት አላቸው ተብለው የተመረጡ ስማርት ስልኮች የትኞቹ ናቸው…ʔ

ስማርት ስልኮችን ተመራጭ ከሚያደርጋው ውስጥ የካሜራ ጥራት አንዱ ነው። የስማርት ስልክ አምራቾች ለካሜራ ጥራት ትኩረት ሰጥው እየሰሩ ይገኛሉ።

https://am.al-ain.com/article/the-best-camera-phone-for-2022?utm_source=paid+twitter&utm_medium=paid+social&utm_campaign=amharic+always+on

የደቡብ ሶዶ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት

  መግቢያ የወረዳው ሳይንስናኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ / ቤት የተቋቋመበት ዋናው ምክንያት በወረዳው የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በማልማትና በሁሉም ስፍራ በስፋት በመጠቀም የህብረተሰቡን ኑ...