ቀን 22/04/2014 ዓ.ም
ኬላ
የደቡብ ሶዶ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት በወረዳው ለሚገኙት ተቋማት (ሴክተሮች) ባለሙያዎች መሠረታዊ የኮምፒዩተር ክህሎት ስልጠና ሰጠ።
የዕለቱን መርሀግብር የደቡብ ሶዶ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ደመላሽ ውዴ ንግግር በማድረግ የጀመሩት ሲሆን ይህ ስልጠና እንደ አዲስ ተቋም ይበል የሚያሰኝ ተግባር ነው፤ ምክንያቱም ልምድ ባላቸው ወረዳዎች ሊሰጥ ያልተቻለውን ይህ መሰረታዊ የኮምፒዩተር ስልጠና በእኛ ወረዳ በአጭር ጊዜ ውስጥ መዘጋጀቱ ተቋሙ ባለሙያውን ብሎም ማኅበረሰቡን ለማገልገል ቆርጦ መነሳቱን ይገልፃል ብለዋል። አክለውም የመንግስት ወጪ የኅብረተሰቡ ወጪ ነውና የወጪ ብክነትን ለመቀነስ ተግባሩ የሚጀምረው እንዲህ ዓይነቱ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ስልጠና በመስጠት ይጀምራል።
ፅ/ቤቱ ከቡኢ ኢንደስትሪያል ኮሌጅ አንድ አሰልጣኝ በመጋበዝ ከፅ/ቤቱ ባለሙያ ጋር በመተባበር ስልጠናው ተሰጥቷል። የፅ/ቤቱ ኃላፊ ለአሰልጣኞቹ ማለትም መ/ር ሀይለሚካኤል እና ለአቶ ናትናኤል ይልማሽዋ እንዲሁም ለነበራቸው የመማር ፍቅር ጉጉት ላሳዩት ለሰልጣኞቹ ምስጋናቸውን ችረዋል።
ሰልጣኞቹ ምንም እንኳን በሙያው መስመር ብንሆንም የረሳንውን እንድናስታውስ ረድቶናል፤ በተጨማሪም አዳዲስ የቴክኖሎጂ ሀሳቦችን እንድናገኝ ጠቅሞናል ሲሎ ሀሳባቸውን በድስታ የገለፁት ሰልጣኞቹ ይህ ስልጠና ቀጣይነት ይኑረው በማለት አስተያየታቸውን ገልፀዋል።
በመጨረሻም የፅ/ቤቱ ኃላፊ ስልጠናው ላይ የነበራቸው ቆይታ እንዴት እንደነበረ በመጠየቅ የወሰዱትን ስልጠና በተቋማቸው እንዲሁም በተሰማሩበት ቦታ በመተግበር ኅብረተሰቡን እንዲያገለግሉ አደራቸውን ለሰልጣኞቹ በመግለፅና ከዚህ በበለጠ ተጠናክሮ ስልጠናው እንደሚቀጥል በመግለፅ የዕለቱን መርሀግብር እንደተቋጨ ገልፀዋል።
ዘገባው የደቡብ ሶዶ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት ነው።
Subscribe to:
Comments (Atom)
የደቡብ ሶዶ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት
መግቢያ የወረዳው ሳይንስናኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ / ቤት የተቋቋመበት ዋናው ምክንያት በወረዳው የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በማልማትና በሁሉም ስፍራ በስፋት በመጠቀም የህብረተሰቡን ኑ...
-
የደቡብ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ የ2014 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ጉባኤ በዲላ ከተማ እያካሄደ ይገኛል፡፡ በመድረኩ የክልል ሴክተር ቢሮ ኃላፊዎች ፣የዞንና የልዩ ወረዳ የተቋሙ መምሪያና ጽ/...
-
🔥40 ሺህ ዛፎችን የሚተክለው ድሮን ኤር ሲድ የተሰኘው የአውስትራሊያ የባዮቴክ ኩባንያ እነዚህ ራሳቸውን ችለው የሚበሩ ድሮኖች ከአየር ላይ በቀን ከ40,000 በላይ የዘር ፍሬዎችን በመትከል የደን ጭፍጨፋን መቋቋም እንደሚ...
-
መግቢያ የወረዳው ሳይንስናኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ / ቤት የተቋቋመበት ዋናው ምክንያት በወረዳው የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በማልማትና በሁሉም ስፍራ በስፋት በመጠቀም የህብረተሰቡን ኑ...