♻️ ቲክቶክ ለወደድነው ቪዲዮ ገንዘብ ቲፕ የምናደርግበት አማራጭ እየሞከረ መሆኑን አስታወቀ።

 


♻️ ቲክቶክ ለወደድነው ቪዲዮ ገንዘብ ቲፕ የምናደርግበት አማራጭ እየሞከረ መሆኑን አስታወቀ።


አዲሱ የቲክቶክ አገልግሎትም በማህበራዊ ትስስሩ ላይ ተጭነው ለወደድነው ምስል ጉርሻ ገንዘብ (ቲፕ) ለመስጠት የሚያስችል መሆኑም ነው የተነገረው። “ቲፕ (tips)” የሚል አማራጭ የሚመጣው አዲሱ አገልግሎት 5፣ 10 እና 15 ዶላር ቲፕ ማደረግ ያስችላል ሲል ዘ ቨርጅ የተባለው ድረ ገፅ አስነብቧል።


ከአማራጮቹ ውጪም ቲፕ ማድረግ የሚፈልግ ሰው ዝቅተኛ ተብሎ ከተቀመጠው 1 ዶላር ጀምሮ እስከፈለገው የገንዘብ መጠን ድረስ ቲፕ ማድረግ የሚችል መሆኑም ታውቋል። በቲክቶክ ላይ በጉርሻ መልክ (ቲፕ) የተሰጠው ገንዘብ ሳይቆራረጥ ለባለ ተንቀሳቃሽ ምስሉ (ቪዲዮ ባለቤት) የሚደርስ መሆኑም ነው የተሰማው።


በቲክቶክ ላይ የጉርሻ (ቲፕስ) ተጠቃሚ ለመሆን ተጠቃሚዎች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች እንዳሉም ኩባንያው አስታውቋል። ከመስፈርቶቹ ውስጥ ተጠቃሚው ቢያንስ 100 ሺህ ተከታዮች ያሉት ሊሆን ይገባል የሚለው ዋነኛው ሲሆን፤ የቲክቶክ የእድሜ መስፈርት ማሟላትም ሌለኛው ነው ተብሏል።


በቲክቶክ ላይ ቲፕ የሚያደርግ ወይም ጉርሻ የሚሰጥ ሰው እድሜው ከ18 ዓመት በላይ መሆን አለበት የሚለውንም ኩባያው በመስፈርትነት አስቀምጧል። የቲክቶክ ቲፕ አገልግሎት አሁን ላይ በሙከራ ደረጃ የተሰወኑ ገጾች ላይ ብቻ መለቀቁ የነገረ ሲሆን፤ በምን ያክል ስፋት እና መቼ ሙሉ በሙሉ ይለቀቃል የሚለው ላይ ግን ኩባያው አስተያየት አልሰጠም።Visit it!!!

 📍የሳምንቱ Technology News📍

፩ YouTube የDislike Buttonኑን ከPublic እይታ ወደ Private ሊቀይር ነው ይሄም ማለት YouTube ላይ የሚለቀቁትን ማንኛውንም Video ተመልካቹ ወይም ግለሰብ Dislike ቢያደርግ ያን Dislike ሌሎች ሰወች ማየት አይችሉም ለChannleሉ ባለቤት ብቻ ይታያል ማለት ነው 👁


YouTube ይሄንን ያደረገበት ምክንያት (Dislike Attackን) ለመከላከል ነው Dislike Attack ማለት አንዳንድ ሰወች በግልም በGroupፕም በመሆን ሆን ብለው አንዳንድ የYouTube Channelሎችን ኢላማ   በማድረግ እዛ Channle ላይ የሚለቀቁትን Video Dislike ያደርጋሉ ይሄ ደግሞ የChannel Creatorች ላይ ከፍተኛ ጮና እያሳደረ በመሆኑ ነው🤕 


፪ የGoogle ኩባንያ ምርት የሆኑት Pixel 6 ና 6 Pro ስልኮች ካሜራቸውን በመጠቀም የስልኩን ባለቤት የልብና የትንፋሽ መጠንን የሚለካ ና የሚከታተል Feature ይዞ መቷል🔥


፫ Apple ና Microsoft ሁለቱም በአሁኑ ጊዜ ዋጋቸው 2.5 ትሪሊዮን💲አካባቢ ነው 😬


፬ የYouTube የማስታወቂያ ገቢው በሦስተኛው ሩብ ዓመት 7.2 ቢሊዮን ዶላር አድርሷል📉


፭ Gmail በአንዳንድ ሀገራት የመቆራረጠ ችግር ገጥሞታል ብዙ ተጠቃሚወችም ችግሩን ለ Google Report እያደረጉ ነው በUS UK ና Europe ያሉ ሰወች የGmail አካውንታቸውን Login ለማድረግ እየተቸገሩ ነው


Google ችግሩን Fix ለማድረግ ተፍ ተፍ እያለ ይገኛል።

የደቡብ ሶዶ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት

  መግቢያ የወረዳው ሳይንስናኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ / ቤት የተቋቋመበት ዋናው ምክንያት በወረዳው የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በማልማትና በሁሉም ስፍራ በስፋት በመጠቀም የህብረተሰቡን ኑ...